ተጠቃሚዎች ያለ ሳተላይት ዲሽ ቴሌቪዥን መመልከት የሚችሉበትን "ቴሌስትሪም" የተሰኘ አገልግሎት ጀምሬያለሁ ብሏል ኢትዮ ቴሌኮም
ኩባንያው የቴሌስትሪም አገልግሎት ተጠቃሚዎች የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ይዘቶችን በቤታቸው ባለው የብሮድባንድ ኢንተርኔት ዋይ ፋይ እንዲመለከቱ ያስችላል ብሏል።
ከ60 በላይ የቀጥታ ስርጭት ቻናሎችን እና ከ3መቶ50 በላይ በፍላጎት የሚታዩ ቪዲዮዎችን መያዙን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።
ቴሌስትሪም ያለ ሳተላይት ዲሽ መቅረቡ የአየር ሁኔታ ሳይበግረው አገልግሎት ለተጠቃሚው እንዲደርስ ያደርጋል ብለዋል።
የቴሌስትሪም አገልግሎት፤ በመደበኛ ብሮድባንድ እና በሲም ካርድ የሚቀርብ ሲሆን፥ ስማርት ያልሆኑ ቴሌቪዥኖችን ወደ ስማርትነት በመቀየር ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል ተብሏል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አገልግሎቱ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለሳተላይት ኪራይ የሚከፍሉትን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት በሀገር ውስጥ መሰረተ-ልማት ስርጭታቸውን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ እንዲያከናውኑ ይረዳቸዋል ብለዋል።
አገልግሎቱ በሀገራችን እስካሁን የነበረውን የሳተላይት ዲሽ ጥገኝነት የሚቀይር አማራጭ ይዞ የመጣ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፤ ስርጭቶችን በአገር ውስጥ በሚገኘው ቴሌ ክላውድ በማስተናገድ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ዜናዎችን፣ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞችን፣ ትምህርታዊ ይዘቶችን፣ ፖድካስቶችን እና ፊልሞችን ያለ ምስል መቆራረጥ ለማስተላለፍ ያስችላል ብለዋል።
አገልግሎቱ በክፍያ የሚሰጥ ሲሆን፥ በአንድ አመት ጊዜ የሚከፈል እንዲሁም ኩባንያው ባዘጋጀው የአጭር ጊዜ የ33 በመቶ ቅናሽ ተጠቃሚ መሆን የሚቻል መሆኑ ተገልጿል።
seledadotio

8 months ago