ፓን አፍሪካ ላይ ያተኮረ ዶክመንተሪ ተመረቀ
#ethiopia | በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን "ICC: Universal Justice Without Universality" ( ዓለም አቀፋዊነት የጎደለው ዓለም አቀፋዊ ፍትህ) የተሰኘ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ የካቲት 6 2018 በቱሊፕ ኦሎምፒያ ሆቴል ተመርቋል።
በዜግነት የጊኒ ተወላጅ የሆነው ታዋቂው ፓን አፍሪካኒስት ፊልም ሰሪ ባካሪ ካንቴ ዶክመንተሪውን ያዘጋጀ ሲሆን ነዋሪነቱም በፈረንሣይ ነው።
በጄኔሲስ ኢንተርቴይመንት የቀረበው ይህ ዘጋቢ ፊልም፣ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) አሰራር፣ ተአማኒነትና የፍትሐዊነት ጥያቄዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው።
የፊልም ባለሙያው ባካሪ ካንቴ በሲኒማቶግራፊ ሙያ ከ 20 አመት በላይ የቆየ ሲሆን ፊልሙንም ለማዘጋጀት 2 አመት ወስዶበታል።
ከአለምአቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሠራር ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ ባለሙያዎችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ የቀረበው ይህ ዘጋቢ ፊልም በጉዳዩ ላይ መረጃ ለሚሹ ሁሉ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነው።
ዶክመንተሪው ለዕይታ በቀረበበት ጊዜ የአፍሪካ ህብረት ባልደረቦችና ሌሎችም የፓን አፍሪካ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ እንግዶች መታደማቸው ታውቋል።
ይህ ለ30 ደቂቃዎች የቆየው ዘጋቢ ፊልም በተለይም ፍርድ ቤቶች ከአፍሪካ አገራት ጋር ያለውን ግንኙነትና "ሁለንተናዊ ፍትህ" በሚለው መርህና በተግባር ባለው ልዩነት ላይ ያተኮሩ ጥልቅ ትንታኔዎችን አካቷል።
የዚህን ዶክመንተሪ ፊልም የምረቃ መርሀ ግብር ከአፍሪካውያን ወንድሞች ጋር በመሆን ያስተባበረው ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን (ዕዝራ እጅጉ) ሲሆን ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለመርሀ ግብሩ መሳካት ትልቁን ድርሻ ወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #africanunion #panafricanism #icc #justiceforafrica #bakarykante #documentary #addisababa #tewodajmedia #africaunited

4 months ago