Logo
Getu Temesgen
🌍 የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት 10 አባላት ተመረጡ! 🇪🇹

​#ethiopia | ሶማሊያ፣ ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ወደ ምክር ቤቱ ተቀላቅለዋል

​በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው 48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ፤ ለአፍሪካ የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት (PSC) ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ 10 ሀገራትን መርጧል።

​የተመረጡት ሀገራት በዞን:
​📍 ምስራቅ አፍሪካ: ሶማሊያ 🇸🇴 እና ዩጋንዳ 🇺🇬

​📍 ማዕከላዊ አፍሪካ: ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 🇨🇩 እና ጋቦን 🇬🇦

​📍 ምዕራብ አፍሪካ: ቤኒን 🇧🇯፣ ኮትዲቯር 🇨🇮 እና ሴራሊዮን 🇸🇱

​📍 ሰሜን አፍሪካ: ሞሮኮ 🇲🇦

​📍 ደቡባዊ አፍሪካ: ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦 እና ሌሴቶ 🇱🇸

​የስራ ዘመን:
እነዚህ ሀገራት እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 1 ቀን 2026 እስከ ማርች 31 ቀን 2028 ድረስ ለሁለት ዓመታት በምክር ቤቱ ያገለግላሉ።

​ቀጣይ ሂደት:
ይህ የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ምርጫ፤ በመጪው ቅዳሜና እሁድ (የካቲት 7 እና 8) በሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ በይፋ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

​ለአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ የበኩላቸውን እንዲወጡ እንመኛለን!

​#africanunion #au #peaceandsecurity #somalia #morocco #southafrica #addisababa #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.