Logo
Getu Temesgen
🌍 "ብሪክስ የተፈጠረው በምዕራባውያን ቁጥጥር ስር ያለውን ዓለም አቀፍ ስርዓት ለመቃወም ነው!"

- የብሪክስ ተማሪዎች ምክር ቤት 🇧🇷🇷🇺🇮🇳🇨🇳🇿🇦

​* የዶላር እጥረት ላለባቸው ሀገራት ብሪክስ ትልቅ እፎይታ ነው
#ethiopia | ​የብሪክስ ተማሪዎች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ታምራት ተስፋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃለ-ምልልስ፤ የብሪክስ መስፋፋት ዋና ምክንያት አሁን ያለው ዓለም አቀፍ ስርዓት በምዕራባውያን ቁጥጥር ስር መውደቁ መሆኑን ገልጸዋል።

​የሉዓላዊነት ጥሰት ማሳያ:

ፕሬዚዳንቱ አሜሪካ በቅርቡ በቬኔዙዌላ ፕሬዚደንት ኒኮላስ ማዱሮ ላይ ያደረገችውን እንቅስቃሴ እንደ ማሳያ በመጥቀስ፤ "የአንድን ሀገር ሉዓላዊነት የደፈጠጠችበት መንገድ ዓለም አቀፍ ስርዓቱ አደጋ ላይ እንደወደቀ ያሳያል" ብለዋል።

​የተቋማት ከአድሎአዊነት:

እንደ ዓለም ባንክ እና የተባበሩት መንግሥታት ያሉ ተቋማት ሁሉንም ሀገራት በእኩልነት ማገልገል ሲገባቸው፤ የምዕራባውያን መሳሪያ መሆናቸው ሀገራት አማራጭ እንዲፈልጉ አስገድዷቸዋል።

​የዶላር ጫና እና መፍትሄው:

ብሪክስ ከዶላር ለመላቀቅ (De-dollarization) የሚያደርገው ጥረት በተለይ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ላለባቸው ታዳጊ ሀገራት ትልቅ ተስፋ ነው። "በሂደት ሀገራት በራሳቸው ገንዘብ መገበያየት ሲጀምሩ በዶላር ላይ ያለው ጥገኝነት እየቀነሰ ይመጣል" ሲሉ ታምራት ተስፋዬ አክለዋል።

​ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

​#brics #geopolitics #economy #dedollarization #ethiopia #sputnikafrica #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.