“እሸቱን ከወዴት አገኘኸው?”
ጌታችን ከሐዋርያት አስቀድሞ ይህን ቅዱስ ታዴዎስን እንደ መረጠው መጽሐፈ ስንክሳር ይናገራል፡፡ እርሱም በየአገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ከአይሁድና ከአረማውያን ወገን ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሶ አጥምቋል፡፡ በማቴ. 10÷3 እንደተጻፈው አባቱ እልፍዮስ ይባላል፡፡ በሉቃስ 6÷16 ደግሞ ሐዋርያው “ታዴዎስ ልብድዮስ”፣ “የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ” ተብሎም ሲጠራ እናያለን፡፡ አንድ ቀን ወደ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሦርያ ለስብከተ ወንጌል ሲሔድ ጌታችን በጐልማሳ አምሳል ተገልጦ “ወዳጄ ታዴዎስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ” ብሎ ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም እንደ አባትነቱ ወደ ሦርያ አብሮት ሔደ፡፡
ከከተማዋ አጠገብ ሲደርሱም አንድ ሽማግሌ በሮችን ጠምደው ሲያርሱ አገኙ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ሽማግሌውን ምግብ ለመናቸው፡፡ ሽማግሌው እስኪመለሱ ቅዱስ ጴጥሮስ ሠላሳ ትልም አረሰ ቅዱስ ታዴዎስም በዚያ የነበረውን የሥንዴ ዘራበት፡፡ የተዘራውም ወዲያዉኑ በቅሎ፣ አድጎ፣ እሸት ኾነ፡፡ ሽማግሌው ምግብ ይዘው ከቤታቸው ሲመለሱም ሐዋርያት ያደረጉትን ተአምር አይተው ደነገጡ፡፡ ከእግራቸው ሥር ወድቀውም “እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን?” አሏቸው፡፡ ሽማግሌውም የሥንዴውን እሸት ይዘው፣ በሬዎቻቸውን እየነዱ ወደ ከተማ ሔዱ፡፡
ሰዎችም ወቅቱ የእርሻ እንጂ የእሸት ጊዜ ስላልነበረ እየተገረሙ “እሸቱን ከወዴት አገኘኸው?” አሏቸው፣ ጉዳዩን ሲያውቁም ከሀገሪቱ ሹማምንትጋር በብዙ አሰቃዩዋቸው፡፡ ቅዱስ ታዴዎስም መጥቶ አስተማራቸው፡፡ በርካቶችም ተጠመቁ፡፡ አንድ ባለጸጋም በእምነት ፈተነው እርሱም ጌታችን እንደተናገረ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ስትሾልክ አሳየው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ወንጌልን በየአገሩ እየተዘዋወረ ሲሰብክ ቆይቶ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሐምሌ 2 ቀን ዐርፏል፡፡
በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ የሚያልፉ ቅዱሳን ገዳማውያንም የሐዋርያትን ፈለግ ተከትለው ዓለምን ንቀዋል፡፡ በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውንም እንደግፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

8 months ago