Logo
Getu Temesgen
አዋሽ ባንክ ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን” በሚል መሪ ቃል የደንበኞች ሳምንት መርሃ-ግብር አስጀመረ
#ethiopia | አዋሽ ባንክ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ለማጎልበት ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን” በሚል መሪ ቃል በዋናው መስሪያ ቤት አሰልጣኝ ጀምሯል።

ባንኩ በሁሉም ቅርንጫፎች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት መርሃ-ግብር ዛሬ የካቲት 02 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት አስጀምሯል።

የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በመርሃ-ግበሩ ማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት ባንኩ ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ የደንበኞቹን ፍላጐት ለማርካት ደንበኞችን ማዕከል ያደረጉ ደንበኛ-ተኮር አገልግሎቶችን እያቀረበ ሰላሳ አንድ ዓመታትን በስኬት መጓዙን ተናግረዋል።

አዋሽ ባንክ ደንበኞቹ ያለብዙ ውጣ ውረድና ልፋት በአቅራቢያቸው እና በሚያመቻቸው የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በቅርንጫፎች ስርጭት ረገድ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረው በአሁኑ ወቅት የባንኩ የቅርንጫፎች ብዛት ከ1000 በላይ መድረሱንም ተናግረዋል፡፡

ከዚሀም ጋር በተያያዘ በቅርቡ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኤጀርሰ ጎሮ ከተማ ለባንኩ ታሪካዊ የሆነውን አንድ ሺህ (1000ኛ) ቅርንጫፉን በታላቅ ድምቀት ማስመረቁንም አቶ ጸሐይ አክለው ተናግረዋል፡፡

አዋሽ ባንክ ደንበኞች በሳምንት ሰባቱንም ቀናት የ24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት የሚያገኙበት ዲጂታል ቅርንጫፎችን በተለያዩ ትላልቅ የሀገራችን ከተሞች ከፍቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋለ።

በተጨማሪም ባንኩ ደረጃቸውን በጠበቁ ዘመናዊ ኤቲኤሞች፣ ፖስ ማሽኖች፣ አዋሽ ብር ፕሮ የሞባይል መተግበሪያ፣ የኤጀንሲ/ወኪል ባንኪንግ እና ኢንተርኔት ባንኪንግ በመታገዝ ቀልጣፋ እና ሁሉን ያማከለ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባንኩ በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ዘርፍ ሰፊ ስራ እየሰራ ሲሆን፣ በባንኩ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ባለፉት 6 ወራት የተከናወነዉ የክፍያ መጠን አንድ ትሪሊየን ብር መድረሱን ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።
#getutemesgen #getu #ጌጡ

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.