ቦትስዋና የኦሊምፒክ ጀግኖቿን በገንዘቧ ላይ አሳተመች
#fastmereja I የቦትስዋና መንግስት በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ አምሳያ የሌለው ድል ላስመዘገቡት ጀግኖቹ ክብር ሲል አዲስ የ 50 ፑላ (P50) የባንክ ኖት በይፋ አውጥቷል።
ለሌትሲሌ ቴቦጎ (Letsile "School-boy" Tebogo)፦ በ200 ሜትር የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ በመሆን ታሪክ ለሰራው ወጣት አትሌት ልዩ እውቅና ተሰጥቶታል።
ለ4 × 400 ሜትር ቡድን በኦሊምፒኩ የብር ሜዳሊያ ላስመዘገቡት የቡድን አባላት ማለትም አንቶኒ ፔሴላ (Anthony Pesela)፣ ባያፖ ዶሪ (Bayapo Ndori) እና ኮሊን ኬቢንትሺፒ (Collen Kebintshipi) ምስላቸው በገንዘቡ ላይ እንዲሰፍር ተደርጓል።
ይህ እርምጃ አትሌቶቹ ለሀገራቸው የፈጠሩትን ብሄራዊ ኩራት ለዘላለም በታሪክ ማህደር ውስጥ ለማኖር የታለመ ነው። በባንክ ኖት ላይ የአትሌቶች ምስል እንዲሰፍር ማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን በጣም ብርቅ እና ከፍተኛው የክብር መግለጫ ነው።
ቦትስዋና ከዚህ ቀደም ለቴቦጎ ድል ማግስት የግማሽ ቀን ብሄራዊ እረፍት ማወጇ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በገንዘቧ ላይ ምስሉን በማተም ለስፖርተኞች ያላትን ታላቅ ክብር ዳግም አሳይታለች። #ስፖርት

4 months ago