Logo
YenetaTube
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በዜጎች መስዋዕትነት እንጂ በዕርዳታ አልተገነባም" — ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ — ኢትዮጵያ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አንድም ሳንቲም የውጭ ዕርዳታም ሆነ ብድር አለመጠቀሟን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ግድቡ የተገነባው በአሜሪካ ገንዘብ ነው" በሚል በተደጋጋሚ ለሚሰጡት መግለጫ ምላሽ በሚመስል መልኩ ነው።

በሕዳሴ ላይ አንድም ብር ዕርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ፕሮጀክቱ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጋራ የቆሙበት የድል አሻራ መሆኑን ገልጸዋል።

* እንዲህ ያለውን ግዙፍ ብሔራዊ ፕሮጀክት ያለምንም የውጭ ድጋፍ ያሳካ መንግሥት "ልማት አይሰራም" ተብሎ ሊታማ አይገባውም ሲሉ ንግግሩን "ግፍ" በማለት ገልጸውታል።

* ግድቡ የኢትዮጵያውያን የቁርጠኝነትና የመጨከን" ውጤት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውበታል።

ይህ ማብራሪያ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ብቃቷንና የገንዘብ ምንጯ የዜጎቿ መዋጮ ብቻ መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በድጋሚ ያረጋገጠ ነው ተብሏል።

Via House of Federation of Ethiopia

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.