መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ጋር ከሚደራደር በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው የሚል ጥያቄ በፓርላማ ተነሳ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላቱ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መስጠት የጀመሩ ሲሆን ከእርሳቸው አስቀድሞ ግን የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል፡፡
በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ የባህር በር፣ ሰላምና ጸጥታ፣ የተፈናቃዮች ሁኔታ፣ ህወሓት፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የፓርላማ አባሉ አበባው ደሳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባነሱት ጥያቄ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር ከሚያባብሱ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው በሀገሪቱ ያለው የሰላም እና የፀጥታ ችግር አለመቀረፍ ነው ብለዋል።
ይህንን ለመቅረፍም የምክር ቤት አባላቱ ለ3 ዓመታት ውትወታ ሲያደርግ እንደነበር ቢከርምም ምንም ዓይነት ለውጥ አለመምጣቱ እንዲሁም መንግስት ከተለያዩ የታጠቁ አካላት ጋር ድርድር እያደረግኩ ነው ቢልም ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪ መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ታጣቂዎች ጋር ከመደራደር ይልቅ በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው? ሲሉም አክለዋል፡፡
የባህር በር ፣ የልማት፣ ሀገራዊ ምክክር እና ምርጫን በተመለከተ መንግስት ያለሠላም እንዴት ለማሳካት አሰበ የሙሉ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሠንዝረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ምላሽ ጀምረዋል፡፡
seledadotio

4 months ago