Logo
FastMereja
ታላቅ የቤተክርስቲያን የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ

ለተከበራችሁ የገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች በሙሉ

በሰሜን ሸዋ ስላሴ ሀገረ ስብከት በአለልቱ ወረዳ ቤ/ክህነት ሥር የሚገኘው የአለልቱ ዘራማ ቅዱስ ገብርኤል ህንፃ ቤ/ክርስቲያን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምስራቅ በደብረብርሃን መውጫ መንገድ በ57 ኪ.ሜትር በዋናው አስፋልት ላይ ይገኛል።

ይህ የቅዱስ ገብርኤል ፅላት ከተለያዩ ንዋየ ቅዱሳት ጋር ግንቦት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ለ300 ዓመታት ተሰውሮ ከነበረበት አለት ድንጋይ ሥር ጊዜው ሲደርስ ወጥቶ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እየተፈፀመበትና ፀበሉም ተአምራትን እየሠራ ይገኛል፡፡ ይህ ህንፃ ቤ/ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፅዑ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ መልካም ፈቃድ ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ በኋላ በቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች ከየአቅየጫው የሚገኙት ምእመናን በቁሳቁስና በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ባዛር በማዘጋጀት በተገኘው ገቢ በከፍተኛ ፍጥነት ህንፃው ለፍፃሜ እየተቃረበ ይገኛል፡፡ በዚህ መልኩ አስተዋፅኦ ላደረጋችሁልን የቤ/ክርስቲያናችን ልጆች ሁሉ ምስጋናችንን በእግዚአብሔር ስም እናቀርባለን።

በእግዚአብሔር አጋዥነት እኛው የጀመርነውን እኛው ጨርሰን ለአገልግሎት ለማብቃት ለመጨረሻ ጊዜ ከጥር 30 ቀን እስከ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቆይ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ባዛር አዘጋጀተን የጀመርነውን እንጨርሰዋለን እግዚአብሔር ቢረዳን በማለት የቀረንን የውስጥና የውጭ ሥራዎች በርብርብ ለመጨረስ በዚህ ኘሮግራም ላይ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ልክ እንደ ትላንቱ ለማድረግ እርስዎም ቤተሰብዎን ወዳጅ ዘመድዎንና ሌሎችንም ምእመናን በማስተባበር የበኩልዎን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱልን በማለት አክብሮታዊ ጥሪያችንን በገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ስም እናቀርባለን።

👉 Commercial Bank of Ethiopia - 1000153993002
👉 Awash Bank - 01321117226200
👉 Coffee Bank - 5559501001063
👉 Dashen Bank - 5811797956011

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.