Logo
SeledaPost
እናት ልጇን በሆስፒታል ጥላ ጠፋች (ሆሳዕና)

በዛሬው ዕለት ከሆሳዕና የተሰማው መረጃ ብዙዎችን እያስቆጣና እያሳዘነ ይገኛል።

አንዲት እናት በሆስፒታል በሰላም ተገላግላ ገና ጥቂት ሰዓታት ሳይሆናት፣ ጨቅላ ልጇን በአልጋ ላይ ጥላ በመሰወሯ ሕፃኑ ያለ ረዳት ቀርቷል።

ለምን?

ይህ ድርጊት እናቶች የሚገጥሟቸውን ከባድ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች በግልጽ የሚያሳይ ነው።

አንዲት እናት ከሆዷ የወጣውን ፍሬ ጥላ እንድትሄድ የሚያደርጋት የልብ ጥንካሬ ሳይሆን፣ ምናልባትም ሊሸከሙት የማይችሉት የመንፈስ ጭንቀት ወይም ማህበራዊ መገለል ሊሆን ይችላል።

ማህበረሰባችን እንዲህ ዓይነት ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት እናቶችን የሚደግፍበትና የሚረዳበት መንገድ ሊዘረጋ ይገባል።

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.