#ሩሲያ ያክ-130 ተዋጊ አውሮፕላኖችን እና ኦሪዮን ድሮን ለ #ኢትዮጵያ ማስረከቧ ተገለፀ‼️
ሩሲያ እስከ ስድስት የሚደርሱ ያክ-130 (Yak-130) የተራቀቁ የማሰልጠኛ እና ቀላል ተዋጊ አውሮፕላኖችን እንዲሁም ቢያንስ አንድ ኦሪዮን የተሰኘ ተዋጊ ድሮን ለኢትዮጵያ ማስረከቧን ‘ዲፌንስ ኤክስፕረስ’ የተሰኘው የዩክሬን የመከላከያ ጉዳዮች ህትመት ዘገበ።
ህትመቱ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ዘገባ፣ አውሮፕላኖቹ እና ድሮኑ በቢሾፍቱ አየር ኃይል ቤዝ በተካሄደው የ2026 አቪዬሽን ኤክስፖ ላይ መታየታቸውን አመልክቷል።
ከዝግጅቱ የተገኙ ምስሎች ከ2301 እስከ 2306 መለያ ቁጥር ያላቸውን ያክ-130 ጄቶች የሚያሳዩ ሲሆን፣ እነዚህ አውሮፕላኖች በዋነኝነት ለአብራሪዎች ስልጠና የተሰሩ ቢሆኑም ቀላል የውጊያ ተልዕኮዎችን የመፈጸም አቅም እንዳላቸው ተጠቁሟል።
እንደ ዲፌንስ ኤክስፕረስ ዘገባ፣ የኦሪዮን ሰው አልባ አውሮፕላን በኢትዮጵያ መታየት የሩሲያ ሰራሹ ምርት በይፋ ለውጭ ሀገር ሲሸጥ የታየበት የመጀመሪያው አጋጣሚ ነው።
ኦሪዮን በመካከለኛ ከፍታ ላይ ለረጅም ሰዓታት መብረር የሚችል ድሮን ሲሆን፣ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ አልፎ አልፎ ለውጊያ ስትጠቀምበት ቆይታለች።
ድሮኑ ቀደም ሲል የቱርክን ባይራክታር ቲቢ2 እና አኪንጂ፣ የኢራንን ሞሃጄር-6 እና የቻይናን ዊንግ ሎንግ 1 ድሮኖችን በባለቤትነት ለያዘችው ኢትዮጵያ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆናት ዘገባው አመልክቷል።
seledadotio

8 months ago