Logo
Getu Temesgen
🚨 ጥብቅ የጥንቃቄ መልዕክት ለዋትሳፕ እና ቴሌግራም ተጠቃሚዎች! 🚨
#ethiopia | ​"የነፃ ኢንተርኔት እና የስብሰባ ሊንኮችን በመላክ የሚደረግ የማጭበርበር ወንጀል ተስፋፍቷል"

​የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፤ በሀገራችን በዋትሳፕ (WhatsApp)፣ በቴሌግራም (Telegram) እና በመሰል ፕላትፎርሞች አማካኝነት የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች መጨመራቸውን አስታውቋል።

​የጥቃቱ ስልት ምን ይመስላል?

አጭበርባሪዎቹ ወቅታዊ ሁኔታዎችን (ለምሳሌ፡ ሲምፖዚየሞችን፣ ኦንላይን ስብሰባዎችን) እንደ ሽፋን በመጠቀም፦

❌ "ለተሳታፊዎች የተዘጋጀ ነጻ የኢንተርኔት ፓኬጅ"፣
❌ "ልዩ የስራ ቅጥር"፣
❌ "ይህ የስብሰባ መሳተፊያ ሊንክ ነው፤ ከፍተው ይግቡ" የሚሉ መልዕክቶችን ይልካሉ።

​አደጋው ምንድን ነው?

ሊንኩን ሲጫኑ አካውንትዎ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር ይውላል። ከዚያም የእርስዎን ማንነት በመጠቀም ለወዳጅ ዘመድ "ድንገተኛ ችግር አጋጥሞኛል ገንዘብ ላኩልኝ" የሚል መልዕክት በመላክ ከፍተኛ ዘረፋ ይፈጽማሉ።

​መፍትሄው፡
1️⃣ Two-Step Verification (የሁለትዮሽ ማረጋገጫ) በአካውንትዎ ላይ አሁኑኑ ይተግብሩ።

2️⃣ ከማይታወቅ ሰው የሚላክ ሊንክ አይክፈቱ።

3️⃣ በስልክዎ የሚገባልዎትን የሚስጥር ኮድ (Verification Code) ለማንም አይስጡ።

​ጥቃት ሲያጋጥምዎ ወይም ጥርጣሬ ሲኖርዎት በነጻ መስመር 933 በመደወል ለኢመደአ ያሳውቁ።

​ለወዳጅዎ በማጋራት ከአደጋው ይታደጉ!

​#insa #cybersecurity #scamalert #telegram #whatsapp #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.