Logo
SeledaPost
አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ቶአ ዮሃንስ ቧያለው በነፃ እንዲሰናበቱ ጠየቁ

የሽብር ወንጀል ተከሳሾቹ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሃንስ ቧያለው፤ ያለመከሰስ መብታቸው ከህግ ውጪ መነሳቱን ለፍርድ ቤት አስረዱ።

ተከሳሾቹ በዐቃቤ ህግ የቀረቡባቸው ማስረጃዎች ውድቅ ተደርገው “በነጻ እንዲሰናበቱ” ጠይቀዋል።

ሁለቱን ተከሳሾች ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፤ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 19፤ 2018 ላስቻለው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ነው።

ችሎቱ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው፤ በዐቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃዎች ላይ በእነ አቶ ዮሃንስ ቧያለው መዝገብ ስር የሽብር ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች የጽሁፍ አስተያየት አጠናቅቀው እንዲያቀርቡ ነበር።

ተከሳሾቹ አስተያየታቸውን እንዲያቀርቡ መጀመሪያ ቀጠሮ ተሰጥቿው የነበረው፤ ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው የችሎት ውሎ ነበር። ሆኖም የተከሳሾቹ አስተያየት በጊዜው ተጠናቅቆ ባለመድረሱ፤ የተከሳሽ ጠበቆች ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ባመለከቱት መሰረት ችሎቱ ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬው የችሎት ውሎ፤ በዐቃቤ ህግ የሰነድ ማስረጃዎች ላይ ተከሳሾቹ ባለ 31 ገጽ ምላሻቸውን በጽሁፍ ለችሎቱ አቅርበዋል።

በዚህ ምላሽ ውስጥ ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል፤ የፌደራል እና የክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሀንስ ያለመከሰስ መብታቸው “ከህግ ውጪ የተፈጸመ ነው” የሚለው ይገኝበታል።

seledadotio
seledadotio
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.