ምንነቱ ካልታወቀ ግብዓት ጋር ተቀላቅሎ የተዘጋጀ እንጀራ ለገበያ ሊያውሉ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ቃሉ
በሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ ጂኔላ ወረዳ በልዩ ስሙ ሚካኤል ሰፈር በተባለ አካባቢ ምንነቱ ካልታወቀ ግብዓት ጋር በመቀላቀል ለመጋገር የተዘጋጀ ሊጥ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ምክትል ዳሬክተር ኮማንደር አብዲ ቶፊቅ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ከማህበረሰቡ ለፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ መሰረት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ወደ ቦታዉ በማምራት ለመጋገር የተዘጋጁ ሊጦች እጅ ከፍንጅ መያዝ መቻሉን ሀላፊው ገልፀዋል።
ምንነቱ ያልታወቀ ባእድ ጋር ተቀላቅሎ በቁጥጥር ስር የዋለው የእንጀራ ሊጥ ናሙና ምርመራ ወደ ኢትዮጵያ የምግብ እና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ተልኳል። የእንጀራ ሊጡ የሚዘጋጅበት ቦታ እጅግ ንፅህና የጎደለው እና ለጤና አደገኛ በሆነ ቦታ በመሆኑ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባገኘው ጥቆማ ወዲያው በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፀዋል።
ማህበረሰቡ ለፖሊስ የሰጠዉን ጥቆማ ምስጋና አቅርበዉ ድርጊቱን በፈፀሙ 2 ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኮማንደር አብዲ ቶፊክ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

8 months ago