Logo
FIDEL POST NEWS
የቀድሞው የአርሰናል ኮከብ አዲስ አበባ ገብቷል

​የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን፣ የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ የቀኝ መስመር ተከላካይ ባካሪ ሳኛ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ይገኛል።

ሳኛ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ለሽርሽር ብቻ ሳይሆን ትልቅ ፋይዳ ካለው ስምምነት ጋር ተያይዞ ነው።

​📌 ለምን መጣ?
ባካሪ ሳኛ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከታዋቂው የጣሊያን የስፖርት ትጥቅ አምራች ማክሮን ጋር ለሚያደርገው የሁለትዮሽ ስምምነት እንደ አምባሳደር ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ትጥቅ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

​🇪🇹 ስለ ኢትዮጵያ ምን አለ?

በአሁኑ ወቅት መኖሪያውን ዱባይ ያደረገው ሳኛ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ቁርኝት ጥልቅ መሆኑን ለኢቲቪ (ETV) በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ገልጿል፦
​ስለ እንጀራ፡ "ከምንም በላይ የኢትዮጵያን እንጀራ እወደዋለሁ!" በማለት ለባህላዊ ምግባችን ያለውን ፍቅር ገልጿል።

​ስለ ወገኖቻችን፡ "ዱባይ ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን ጓደኞች አሉኝ። ስለ ሀገሪቱ ብዙ እንዳውቅ የረዱኝ እነሱ ናቸው።"

​ስለ ዋሊያዎቹ፡ "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ተመልክቻለሁ፤ በጣም ጥሩ እና ተስፋ ያለው ቡድን አላችሁ። የዚህ ትልቅ ታሪክ አካል ሆኜ አዲስ አበባ በመምጣቴ ኩራት ይሰማኛል" ብሏል።

​⚽️ የባካሪ ሳኛ አጭር ታሪክ፡
​ለአርሰናል ከ280 በላይ ጨዋታዎችን አድርጓል።

​ከአርሰናል ጋር የኤፍ ኤ ካፕ ( ዋንጫን አንስቷል።

​ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን 65 ጨዋታዎችን ተሰልፎ ተጫውቷል።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.