በአዲስ አበባ የተሽከርካሪዎች ዋጋ ባለፉት ሶስት ወራት በከፍተኛ ሁኔታ መናሩ ተገለፀ
👉 በአንድ መኪና ላይ እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጭማሪ ታይቷል
በመዲናዋ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ በተሽከርካሪዎች መሸጫ ዋጋ ላይ ታይቶ የማይታወቅ እና ገበያውን ያናወጠ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መመዝገቡን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ገልፀዋል።እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ፣ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በተለይም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ከ500 ሺሕ ብር እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
ለዚህ የዋጋ ንረት እንደ ማሳያ የሚጠቀሰውና በከተማዋ በስፋት የሚታየው የቢዋይዲ ሴጉል (BYD Seagull) የኤሌክትሪክ መኪና፣6 ከሦስት ወራት በፊት ከ2.4 እስከy 2.5 ሚሊዮን ብር ይሸጥ የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት እስከ 1 ሚሊዮን ብር በሚደርስ ጭማሪ በማሳየት 3.4 ሚሊዮን ብር እየተሸጠ ይገኛል። በተመሳሳይ የዩዋን-አፕ (YuanUp) የተሽከርካሪ ምርት ቀድሞ ከነበረበት 3.6 ሚሊዮን ብር ወደ 4.8 ሚሊዮን ብር ከፍ ብሏል። ይህ የዋጋ ጭማሪ እንደ መኪናው ዓይነት፣ ሞዴልና ደረጃ ከዚህም በላይ ሊሄድ እንደሚችል ተጠቁሟል።
ለዚህ አስደንጋጭ የዋጋ ጭማሪ ዋነኛ ምክንያቶች ተብለው የተጠቀሱት ደግሞ የዶላር ምንዛሬ ዋጋ መጨመር እና የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዋነኛ ምንጭ የሆነችው ቻይና ከመኪና ኤክስፖርት ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ያደረገችው አዲስ መመሪያ ነው።በገበያው ላይ ከፍተኛ የሆነ የመኪና ፍላጎት መኖሩን የሚገልጹት የዘርፉ ተዋናዮች፣ ዋጋው ቢጨምርም የገዢው ቁጥር ግን አሁንም ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ።
በአንጻሩ በነዳጅ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ጭማሪ ቢኖርም፣ አሮጌ የነዳጅ መኪና ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ መከልከሉና ካለው ከፍተኛ ዋጋ ጋር ተዳምሮ የነዳጅ መኪና ገበያው እንዲቀዛቀዝ እንዳደረገው ተገልጿል።በአሁኑ ወቅት በገበያው ላይ እንደ ቢዋይዲ ኢቱ (BYD E2)፣ ዩዋን አፕ እና ሶንግ ፕላስ ያሉ ሞዴሎች በስፋት እየተሸጡ ቢሆንም፣ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው ሴጉል እና ኢቱ የመኪና ዓይነቶች ግን በገበያው ላይ እጥረት እየታየባቸው መሆኑ ተነግሯል።
መንግሥት አሮጌ የነዳጅ መኪኖችy ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ የጣለው እገዳ ተጠቃሚው ወደ ኤሌክትሪክ መኪና መጠቀሙን ምርጫ የሌለው አማራጭ ቢያደርገውም፣ በየጊዜው የሚጨምረው ዋጋ ግን ለኅብረተሰቡ ትልቅ ፈተና እየሆነ እንደሚገኝ ብስራት ሬድዮ ያነጋገራቸው በመኪና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ተናግረዋል።
seledadotio

7 months ago