ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ታሪካዊውን ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ገዛ
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢትዮጵያ የሆቴል ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለውን ድርሻ የሚያሰፋ ሌላ ትልቅ ግዢ መፈጸሙ ተረጋገጠ። የኢንቨስትመንት ግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ እና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን የሽያጭ ስምምነቱን ዛሬ ተፈራርመዋል።
1. የከተማዋን ገፅታ የሚቀይር ኢንቨስትመንት፡
ዋቢ ሸበሌ ሆቴል በአዲስ አበባ መሃል ከተማ (Mexico/Lideta) የሚገኝ በመሆኑ፣ እድሳቱ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ከማነቃቃቱም በላይ ለከተማዋ ውበት ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ሆቴሉ ወደ "ማሪዮት" ደረጃ ሲያድግ የውጭ ምንዛሬ ግኝትንም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።
2. የሥነ-ህንፃ ጥበብ ጥበቃ፡
ሆቴሉ በ1960ዎቹ የተገነባው በታዋቂ ፈረንሳውያን አርክቴክቶች እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የሚድሮክ እድሳት የሆቴሉን ጥንታዊና ታሪካዊ የሥነ-ህንፃ ቅርፅ (Unique Architecture) ሳይሸረሽር ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ብቻ የማካተት ዓላማ እንዳለው ተጠቁሟል።
3. የሥራ ዕድል ፈጠራ፡
ከፍተኛ በጀት የሚፈጀው ይኸው የማዘመን ፕሮጀክት፣ በግንባታው ወቅት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም ባለፈ፣ ሆቴሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፍ የሆቴል አገልግሎት ደረጃ ሥልጠና የሚያገኙበትና የሚቀጠሩበት ዕድል ይፈጥራል።
4. ለ32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) ዝግጅት፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው ታላቁ COP32 ጉባኤ በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን የሚስብ በመሆኑ፣ ዋቢ ሸበሌ ይህን ኃላፊነት ለመወጣት ከሚዘጋጁ ቀዳሚ ሆቴሎች አንዱ ሆኗል።
ዋቢ ሸበሌ የተገነባው በግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ መልካም ፈቃድ ለልዑል መኮንን ልጆች መተዳደሪያ ነበር።
ሆቴሉ በታሪኩ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ታዋቂ ዲፕሎማቶችን ያስተናገደ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ምልክት ነው።
"የዋቤ ሸበሌን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለትውልድ ለማሻገር በመስማማቱ ሚድሮክን እናመሰግናለን።" — ልዑል በዕደማርያም መኮንን
ሚድሮክ ግሩፕ ባለፈው ሳምንት የመረቀውን "ደንቢ ኤኮ ሎጅ" ጨምሮ፣ በሸራተን አዲስ እና በሌሎችም ታዋቂ ሆቴሎች ያለው ልምድ ለዋቢ ሸበሌ ስኬት ትልቅ ዋስትና እንደሚሆን ይታመናል።

9 months ago