Logo
Getu Temesgen
🙌 በድንጋይ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከተማ - ቅድስት ላሊበላ የጥምቀት ድባብ! 🇪🇹
#ethiopia | ​"በርካታ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች በላሊበላ የጥምቀት በዓልን እያከበሩ ነው"

​የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በዓለም ቅርስነት በተመዘገበችው እና የጥምቀት በዓል ከሚከበርባቸው ምርጥ ስፍራዎች አንዷ በሆነችው ቅድስት ላሊበላ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

​የበዓሉ ትዕይንት፡
በዓሉን ለማክበር የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በያሬዳዊ ዝማሬ አድምቀውታል።

​ልዩ የሚያደርገው ደግሞ፤ ቁጥራቸው በርከት ያሉ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች (Tourists) በዚህ መንፈሳዊ እና ታሪካዊ ክስተት ላይ በመገኘት የላሊበላን ድምቀት እየታደሙ መሆኑ ነው። ላሊበላ ነጭ ለብሳ፣ በእንግዶች ተከባ፣ በዝማሬ ደምቃለች!

​እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

​#lalibela #timket2018 #epiphany #visitamhara #ethiopia #landoforigins #tourism #orthodox

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.