Logo
Getu Temesgen
🏆 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምስራቅ አፍሪካ 1ኛ ደረጃን ያዘ! 🇪🇹🎓
#ethiopia | ​"የ75 ዓመት የዕውቀት ጎታው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጠናውን መራ!"

​ሰሞኑን 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ በዘንድሮው የ"QS World University Rankings" መሰረት ከምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 1ኛ ደረጃን በመያዝ አኩሪ ድል አስመዝግቧል።

​የምስራቅ አፍሪካ "Top 4" ደረጃ:

1️⃣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ኢትዮጵያ) 🇪🇹
2️⃣ ማካሬሬ ዩኒቨርሲቲ (ዩጋንዳ) 🇺🇬
3️⃣ ናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ (ኬንያ) 🇰🇪
4️⃣ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካርቱም (ሱዳን) 🇸🇩

​ለምን ተመረጠ?
እንደ አፍሪካን ኢንሳይደር ዘገባ፤ ደረጃው የተሰጠው በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እና በቀጠናው ልማት ላይ ባበረከቱት አስተዋፅኦ ነው።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለይም በሂውማኒቲስ፣ በሶሻል ሳይንስ፣ በኢንጂነሪንግ እና በጤና ሳይንስ ዘርፎች በሰራቸው ጠንካራ ስራዎች ቀዳሚ ሊሆን ችሏል።

​ለ75 ዓመታት የኢትዮጵያ የዕውቀት የጀርባ አጥንት ሆኖ ፖሊሲ አውጪዎችን እና ምሁራንን ያፈራው ተቋማችን እንኳን ደስ አለህ!

​የዚህ ታላቅ ተቋም ምሩቃን እና ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! 👏

​#aau #addisababauniversity #numberone #eastafrica #education #ethiopia #qsworldranking #75thanniversary

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.