Logo
Getu Temesgen
🙏 "ፈጣሪ ሙሉ ለሙሉ እንዲፈውስህ ፀሎታችን ነው!" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ethiopia | ​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በበጎ አድራጎት ስራዎቹ የሚታወቀውን ማስተር አብነት ከበደን ጠይቀው አጽናንተዋል።

​ከንቲባዋ በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ማስተር አብነት ለወጣቶች ያለውን ተምሳሌትነት በመግለጽ እንዲህ ብለዋል፦

​"በማህበራዊ በጎ አድራጎት ስራህ ለብዙ ወጣቶች ምሳሌ የሆንከው ማስተር አብነት ከበደ፤ ፈጣሪ አምላክ ሙሉ ለሙሉ እንዲፈውስህ ፀሎታችን ነው። ያንተ አርአያነት በርካታ በጎ አድራጊ ወጣቶችን ማፍራት የሚያስችል ነው።"

​ማስተር አብነት በብዙዎች ዘንድ ለተቸገሩ ወገኖች በመድረስ እና በተለይም በጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን በማንሳት የሚታወቅ ቅን ኢትዮጵያዊ ነው።

​ምህረቱን ይላክለት! 🙏❤️

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

​#masterabinetkebede #adanechabebe #getwellsoon #ethiopia #charity #rolemodel

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.