Logo
Getu Temesgen
🎗️ በኢትዮጵያ የሕፃናት የካንሰር መሞትን ለመታደግ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ

📌"ማንም ሕፃን በካንሰር ምክንያት መሞት የለበትም"
#ethiopia | በኢትዮጵያ በየዓመቱ እስከ 8,000 የሚደርሱ ሕፃናት በካንሰር በሽታ እንደሚጠቁ ቢገመትም፣ የሕክምና ዕድል የሚያገኙት ግን ከሩብ በታች (2,000 ያነሱ) መሆናቸው ይታወቃል። ይህንን አሳሳቢ ክፍተት ለመሙላት እና የሕፃናትን ሞት ለመቀነስ ያለመው የኢትዮጵያ የሕፃናት ደም እና ካንሰር ሕክምና ማኅበር (ESPHO) ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በይፋ ተመስርቷል።

📊 የችግሩ ስፋት እና የማኅበሩ ራዕይ

በበለፀጉ ሀገራት የሕፃናት ካንሰር የመዳን ምጣኔ 85% ቢደርስም፣ በኢትዮጵያ ግን በግንዛቤ እጥረት እና በምርመራ መዘግየት ምክንያት አሁንም ውጤቱ እጅግ ዝቅተኛ ነው።

አብዛኞቹ ሕፃናት ወደ ሕክምና ተቋም የሚመጡት በሽታው በጠናበት (ደረጃ 3 ወይም 4) ላይ መሆኑ የሕይወት መታደግ ጥረቱን ፈታኝ አድርጎታል።

ማኅበሩ ይህንን ምስቅልቅል ለመቀየር የሚከተሉትን ግቦች ሰንቋል፦

* ቀድሞ ምርመራ፦ ሕፃናት በሽታው ሳይጸናባቸው ወደ ሕክምና እንዲመጡ ግንዛቤ መፍጠር።

* ወጥ ሕክምና፦ በመላ ሀገሪቱ ጥራት ያለውና ፍትሃዊ የሕክምና አገልግሎት እንዲዳረስ መስራት።

* ምርምርና ስልጠና፦ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን አቅም ማሳደግና በመረጃ ላይ የተደገፈ ሕክምና መስጠት።

🤝 ዓለም አቀፍ ትብብር እና ተስፋ

በምስረታው ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና የ "ሲኦፕ አፍሪካ" ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጄኒፈር ጊል የቸገኙ ሲሆን የፕሮፌሰሯ መገኘት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሕፃናት ካንሰር ሕክምና ያላትን ሚና የሚያጎላ ሲሆን፣ ሀገራችን የ2027ቱን የሲኦፕ አፍሪካ (SIOP Africa) ጉባኤ እንድታስተናግድም ፍላጎት እንዳላት ተገልጿል።

💬 ከአመራሮቹ አንደበት

"የማኅበሩ መመስረት የሕፃናትን ስቃይ ለመቀነስ ያለብንን ሙያዊና ሞራላዊ ግዴታ ለመወጣት ትልቅ አቅም ይፈጥራል።" — ዶ/ር አቤል ኃይሉ (የማኅበሩ ፕሬዝዳንት)

"አላስፈላጊ ስቃይን የምናስቆምበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መጻፍ አለብን።" — ሌሊሴ ዱጋ (ብሔራዊ የክብር አምባሳደር)

🎯 የ2030 ግብ

ይህ ንቅናቄ እ.ኤ.አ. በ2030 የሕፃናት ካንሰር የመዳን ምጣኔን ወደ 60% ለማድረስ የተቀመጠውን ዓለም አቀፍ ግብ ለማሳካት የኢትዮጵያ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

ማኅበሩ ከሕክምናው ባሻገር ለቤተሰቦች ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ በመስጠት ሕክምናን አቋርጦ የመሄድ ችግርን ለመቅረፍም በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስታውቋል።

​Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ኢትዮጵያ #የሕፃናትካንሰር #ጤና #espho #ካንሰር #የሕፃናትጤና #ጤናሚኒስቴር #የደምካንሰር #ethiopia #childhoodcancer

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.