Logo
Getu Temesgen
🌼 መልካም የ"ቢስት ባር" በዓል! 🌼
#ethiopia | ​የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው!

​"ቢስት ባር" የቤንች ብሔር አርሶ አደሩ ጎተራና ሌማቱ ሲሞላ፤ ጥርን ተከትሎ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሻገሩን የሚያበስርበት ታላቅ በዓል ነው።

​የበዓሉ ሦስት ምሰሶዎች፡-

​ምስጋና እና ብኩርና ("ቢስት"): "ቢስት" ማለት የበኩር ማለት ሲሆን፤ አዲሱን የእህል ምርት በቤተሰብ ውስጥ በዕድሜ ትልቅ የሆነው (አያት ወይም አባት) ቀድሞ ይቀምሳል። ይህም ለታላላቆች የሚሰጠውን ክብር ያሳያል።

​አብሮነት: በቤንች ባህል ብቻ መብላት ነውር ነው። ቀድሞ እህል የደረሰለት ለጎረቤቱ የማካፈል ግዴታ አለበት።

​ይቅርታ: በዓሉ የሰላም ነው፤ ቂም ይዞ ማክበር አይቻልም። የተጣላ ካለ በአባቶች ፊት ታርቆ በፍቅር ወደ አዲሱ ዘመን ይሸጋገራል።

​ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው ይህ ድንቅ በዓል፤ ዘንድሮ በሚዛን አማን ከተማ ለ3ኛ ጊዜ በድምቀት እየተከበረ ነው።

​እንኳን አደረሳችሁ! መልካም በዓል!

ጋዜጠኛ ዕድሉ ፈቀደ

​#bistbar #bench #culture #newyear #thanksgiving #ethiopia #mizanaman

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.