Logo
FastMereja
ለ50 ህጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ጥገና ለማድረግ የጋራ ስምምነት ተደረገ

አላማውን በኢትዮጵያ ያሉ ህጻናትን ለማከም በኢትዮጵያ የተቋቋመው እና በአሜሪካ የተመዘገበው ህጻናት አድን የሆነው የልብ ለልብ የህፃናት እርዳታ ፋውንዴሽን (Heart to Heart Children's Aid Foundation) በጣሊያን ሀገር ከሚገኙ 3 ካምፖዎች ጋራ አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ዛሬ ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮ ኢስታምቡል አጠቃላይ ሆስፒታል አከናወነ።

መሰረታቸውን በጣሊያን ያደረጉት ድርጅቶች ማለትም Una per Voce Padre Pio ፣ CCPM እና REBEL Hert'sን በፕሬዚዳንትነት የሚመሩት ሚስተር ኢንዞ ፓሉምቦ በኢትዮጵያ በሚገኘው በኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተው ጉብኝት አድርገው ለ50 የልብ ህሙማን ህጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ጥገና በሚያዝያ ወር ጀምሮ ለመስጠትና በቀጣይም ዘለቄታ ያለው አብሮ መሥራት የሚያስችል ስምምነት ፈጽመዋል። ስምምነቱ ለረጅም ዓመት የሚቆይና በዓመት ሁለት ጊዜ ለሀምሳ 50 ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ሕክምና ለማከናወን የሚያስችል ነው።

በስምምነታቸው መሠረትም በሚያዝያ ወር የተሟላ የሕክምና ቡድን እና የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎችን በመያዝ ለ50 ህጻናቶችን ነጻ የልብ ቀዶ ጥገናና በኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል መስጠት እንደሚጀምሩ ይፋ ሆኗል።

ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ 17 ፕሮፌሽናል ባለሙያዎችን ይዞ በመምጣት በሁለት ተከታታይ ዓመታት ለህጻናቱ ነጻ የልብ ቀዶ ጥገናና ድጋፍ ይሰጣል ሲሉ የ Una per Voce Padre Pio ፕሬዚዳንት ሚስተር ኤንዞ ፓሉምቦ ተናግረዋል።

Heart to Heart Children's Aid Foundation የተቋቋመበት ዋና አላማ በልብ ህመም ምክንያት የሚሰቃዩና ሕጻናት ተገቢውን የሕክምና እርዳታ እንዲያገኙ ለመደገፍ ታስቦ መሆኑን የፋውንዴሽኑ መስራች በአቶ ብርሀን ተድላ ተናግረዋል።

ቀዶ ጥገና የሚደረግላቸው 50 ህጻናቶች የገና (የክሪስማስ) በዓል ስለሆነ በዛሬው ዕለት ጥር 1/2018 ዓ/ም የክሪስማስ ጊፍት ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል ሲሉ የHeart to Heart Children's Aid Foundation መስራች እና የኢትዮ ኢስታምቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ባለቤት አቶ ብርሃን ተድላ ተናግረዋል።

እንዲህ አይነቱ ድጋፍ ሕክምና በወቅቱ ባለማግኘታቸው ምክንያት የሚሞቱ የልብ ሕሙማንን ችግር ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው አቶ ብርሃን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም አቶ ብርሃን ተድላ ልብ ለልብ ችልድረንስ ኤይድ እንዲቋቋም የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጉ ወገኖችና ለኢትዮ ኢስታምቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞችና የቦርድ አካላት ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል።

ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ከ85 በላይ የልብ ሕሙማን ሕፃናት እንዲረዱ ማድረጉን ያስታወሱት አቶ ብርሃን እንደጤና ሚኒስቴር ያሉ አካላት ድጋፍ ወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.