Logo
Getu Temesgen
❤️ የገና ስጦታ ለህጻናት!
ለ50 ህጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ስምምነት ተፈረመ
#ethiopia | ​በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ የሚንቀሳቀሰው "ልብ ለልብ የህፃናት እርዳታ ፋውንዴሽን" (Heart to Heart Children's Aid Foundation) ከሶስት የጣሊያን ግብረ-ሰኖች ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያውያን ህጻናት የህይወት ተስፋ የሚሆን ስምምነት በዛሬው ዕለት ፈጽሟል።

​የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

✅ ምን? ለ50 ህጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ጥገና ለማድረግ።

✅ መቼ? ከፊታችን ሚያዚያ ወር ጀምሮ የሚተገበር ሲሆን፤ በዓመት ሁለት ጊዜ ለ50፣ ለ50 ህጻናት (በድምሩ ለ100) ቀዶ ጥገናው ይደረጋል።

✅ ማን? ስምምነቱ የተደረገው ከጣሊያኖቹ Una per Voce Padre Pio፣ CCPM እና REBEL Hearts ድርጅቶች ጋር ሲሆን፤ 17 ፕሮፌሽናል ዶክተሮች እና የህክምና መሳሪያዎችን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

✅ ቦታ፡ ህክምናው የሚሰጠው በ ኢትዮ ኢስታምቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ነው።

​ልዩ የገና ስጦታ
ዛሬ በተደረገው ስነስርዓት ላይ ለህክምናው የተመረጡት 50 ህጻናት "የገና (የክሪስማስ) ጊፍት ሰርተፍኬት" ተበርክቶላቸዋል።

​የፋውንዴሽኑ መስራች እና የሆስፒታሉ ባለቤት አቶ ብርሃን ተድላ፤ ተቋሙ እስካሁን ከ85 በላይ ህጻናትን መርዳቱን ጠቅሰው፤ ይህ ስምምነት በህክምና እጦት ምክንያት የሚሞቱ ህጻናትን ለመታደግ ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል።

​ፈጣሪ በህክምናው ለሚሳተፉ እጆች ጥበብን ይስጥልን! 🙏

​#hearttoheart #freesurgery #ethiopia #italy #charity #ethioistanbulhospital #goodnews

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.