Logo
FastMereja
ራይድ ለደንበኞቹ የመኖሪያ የቤት ሽልማት አበረከተ ::

Hybrid Designs(ራይድ) ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ ባስጀመረው የሎተሪ መርሃ ግብር አሸናፊ ለሆኑ ደንበኞች የመኖሪያ ቤት ሽልማትን አበርክቷል::
የራይድ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ድርጀቱ እንዲህ ዓይነት የሎተሪ መርሃ ግብሮችን የሚያዘጋጀው የደንበኞቹን ሕይወት በተሻለ መልኩ ለመቀየር ካለው ራዕይ በመነሳት መሆኑን ገልፀዋል ::

"ራይድ ማንኛውንም ዓይነት ኢኒሼቲቭ ይዞ ሲመጣ የሰውን ሕይወት መቀየር አለበት ብለን እናምናለን " ያሉት ሥራ አስኪያጇ የሎተሪው ዋና ዓላማም የአሸናፊዎችን የቤት ኪራይ እና መሰል ወጪዎችን በማቃለል ደንበኞቻችን የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ማስቻል መሆኑንም አስረድተዋል :: በመርሃ ግብሩ የቤት ባለቤት የሆኑት ወይዘሮ ሕይወት ደበላ ለሽልማት ያበቃቸውን የመኖሪያ ቤት ቁልፍ ተረክበዋል :: የመኖሪያ ቤት አሸናፊዋ ከሶስትና ከአራት ዓመታት በላይ የራይድ ትራንስፖርት ደንበኛ እንደነበሩ ጠቅሰዋል ::

ድርጅቱ ይህ የሽልማት መርሃ -ግብር በዚህ እንደማያበቃ እና ወደፊትም በሌሎች የተሻሉ ዝግጅቶች እንደሚቀጥል አስታውቋል ::
ራይድ በቀጣይ የሚኖሩትን እንደዚህ ዓይነት አበረታች ዝግጅቶች እንዲሁም የሚቆዩበትን ጊዜና የሽልማት ዓይነቶችን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግም ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ አስታውሰዋል ::

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.