ትራምፕ ቬንዙዌላ ከ30 እስከ 50 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለአሜሪካ እንደምታስረክብ አወጁ
"ገንዘቡን እኔው ራሴ አስተዳድረዋለሁ!" - ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ትሩዝ ሶሻል" (Truth Social) በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባወጡት መግለጫ፤ የቬንዙዌላ ጊዜያዊ ባለስልጣናት ከ30 እስከ 50 ሚሊዮን በርሜል የሚደርስ ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ለአሜሪካ ለማስረከብ መስማማታቸውን ገልጸዋል።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-
🛢 የነዳጁ መጠንና አይነት፡
ከ30 እስከ 50 ሚሊዮን በርሜል የሚደርስ ከፍተኛ ጥራት ያለው እና ከዚህ ቀደም ማዕቀብ ተጥሎበት የነበረ የነዳጅ ዘይት ነው።
💰 የገንዘብ አስተዳደር፡
ትራምፕ እንደገለጹት፤ ነዳጁ በወቅቱ የገበያ ዋጋ የሚሸጥ ሲሆን፤ "ገንዘቡ ለቬንዙዌላ እና ለአሜሪካ ህዝቦች ጥቅም መዋሉን ለማረጋገጥ እኔው ራሴ እንደ አሜሪካ ፕሬዝዳንትነቴ አስተዳድረዋለሁ (Control)" ብለዋል።
🚢 አፈፃፀም እና ሎጅስቲክስ፡
ፕሬዝዳንቱ የኢነርጂ ሚኒስትሩን ክሪስ ራይት (Chris Wright) ይህንን እቅድ በአስቸኳይ እንዲያስፈጽሙ አዘዋል።
ነዳጁ በማከማቻ መርከቦች ተጭኖ በቀጥታ ወደ አሜሪካ የማውረጃ ወደቦች ይጓጓዛል።
ይህ እርምጃ በአሜሪካ እና በቬንዙዌላ መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም የዓለምን የነዳጅ ገበያ ምን መልክ እንደሚያስይዘው በጉጉት ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#donaldtrump #venezuela #oildeal #breakingnews #usa #energy #chriswright

7 months ago