በኢትዮጵያ ግዙፍ የተባለው የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት በ340 ሚሊዮን ዶላር በጀት ግንባታ ሊጀምር ነው
ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ የሚገኘው የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ለግንባታ የሚያስፈልገውን 340 ሚሊዮን ዶላር ፋይናንስ በማጠናቀቁ ወደ ሥራ ለመግባት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለጸ።
ይህ ግዙፍ የፋይናንስ ጥቅል ከአፍሪካ የልማት አበዳሪ ተቋማት የተገኘ 240 ሚሊዮን ዶላር የረጅም ጊዜ ብድር እና ከኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሁም ከሌሎች ባለሀብቶች የተሰበሰበ 100 ሚሊዮን ዶላር የካፒታል መዋጮን ያካተተ ነው።
የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነው የኬፊ ወርቅ እና ኮፐር (KEFI Gold and Copper) ሥራ አስፈጻሚ ሃሪ አናኖስታራስ-አዳምስ እንደገለጹት፣ የብድር ስምምነቱ መፈረሙ በሳይቱ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ያፋጠነው ሲሆን፣ የወርቅ ዋጋ በዓለም ገበያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ባለበት በዚህ ወቅት ፕሮጀክቱን ማስጀመር ለሀገሪቱ ትልቅ ፋይዳ አለው።
ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ 360 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ማዕድን በፈረንጆቹ 2027 የንግድ ምርት ሥራ ሲጀምር፣ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ዓመታት ውስጥ በዓመት በአማካይ 164,000 አውንስ ወርቅ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።
በአሁኑ ወቅት የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ የመንገድ እና የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎች የተጀመሩ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ ለሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እንደሚሆን ይታመናል።
seledadotio

10 months ago