Logo
FastMereja
8ኛው 'የባለ ራዕይ ሴት' የዕዉቅና መርሀ-ግብር ተካሄደ!
#fastmereja : ሴቶች ከቤተሰብ ምሥረታ እስከ ማህበረሰብ ግንባታ ድረስ ላበረከቱት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እና ሚና ዕውቅና በመስጠት በሌሎች ሴቶች ዘንድ መነቃቃትን የመፍጠር ዓላማ አንግቦ “ባለ ራዕይ ሴት" በሚል መሪ-ቃል የዕውቅና እና ሽልማት ስነስርዓት ተከናዉኗል።

ዘንድሮ ለ8ተኛ ጊዜ በተካሄደው መርሀ-ግብር ራዕያቸውን ተገንዝበው፣ ለትውልድና ለሀገር የላቀና የሚታይ አስተዋጾ ያበረከቱ ተምሳሌት ሴቶችን ነዉ በዛሬዉ እለት የተሸለሙት።

የዘንድሮው 'ዕንቁ ሴት ንቁ ሴት' መርሀ ግብር መሪ ቃል ባለ ራዕይ ሴት የሚል ሲሆን መሪ ቃሉ ወደፊት አዳዲስ ራዕይ የሰነቁ ወጣቶችንም የማነቃቃት ዓላማ እንዳለው ተገልጿል።

በዚህ ታላቅ የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ፣ አዝናኝ መሰናዶዎች የቀረበ ሲሆን ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ እና ዶክተር ሮዳስ ታደሠ አስተማሪ አበረታች መልዕክቶችን አጋርተዋል።

የዕንቁ ኢቬንትስ ሀሳብ አመንጪና ባለራዕይ የሸጋ ትውልድ መሥራችና የከፍተኛ ተቋም መምህር አቶ ሳሙኤል ገረመው ይህን የዕውቅና አሰጣጥ የሚከታተል የዝግጅት ቦርድ ተዋቅሮ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን ገልፆ ለዘንድሮ መከበር ያለባቸውን 1ዐ ሴቶች እንደሸለመ ገልጿል።

የዕንቁ ሴት የበላይ ጠባቂ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ሲሆኑ ሰፊ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎችም በዕንቁ ሴት የሽልማት ዝግጅት ላይ ልዩ ተሳትፎ አድርገዋል።

በዛሬዉ እለት የእዉቅና እና ሽልማት የተበረከተላቸዉ ዕንቁ ሴቶች:-

📌 ዶ/ር ትዕግስት በጤና ዘርፍ
📌 አበበች አፈወርቅ የህይወት ዘመን ሽልማት
📌 ሀናን ማህሙድ ከበጎ አድራጎት ማህበር
📌 በሻቱ ቶለማርያም ከሚዲያና ጋዜጠኝነት
📌 አርቲስት መሠረት መብራቴ በኪነ ጥበብ
📌 ዲዛይነር ሔዋን ቀለመ ወርቅ ከሥራ ፈጠራ
📌 ሣምራዊት መሐመድ ከወጣት ባለራዕይ
📌 ልዕልት አንድሮሜዳ ከኢትዮጵያ
📌 ገነት ገ/ሥላሴ ከልመና ወደ ሽመና
📌 ዶክተር ሀመልማል መንግሥቱ

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.