Logo
Getu Temesgen
አሐዱ ባንክ የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ 7ኛውን የደም ልገሳ መርሐ ግብር አካሄደ
#ethiopia | ​አሐዱ ባንክ የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ፤ ከ"ሳሮ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን" ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን 7ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሐ ግብር ዛሬ ታኅሣሥ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. አከናወነ።

​ባንኩ "ሰብአዊነት" (Humanity) ብሎ ከለያቸው ስድስት ዐበይት ተቋማዊ እሴቶቹ መካከል አንዱን በተግባር ለማዋል እና የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ያለመው ይህ መርሐ ግብር፤ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በድምቀት ተካሂዷል።

​በዚሁ የልገሳ መርሐ ግብር ላይ የአሐዱ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች፣ ሠራተኞች እንዲሁም የሳሮ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን ኃላፊዎች በመገኘት ደም ለግሰዋል።

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.