Logo
SeledaPost
የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ንድፍ ተጠናቀቀ፤ ግንባታው በጥር ወር ይጀመራል ተብሏል

💵 ለግንባታ ከሚያስፈልገው 10 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 20 በመቶውን አየር መንገዱ ሊሸፈን፤ ከ80 በመቶ ውስጥ የአፍሪካ ልማት ባንክ 500 ሚሊዮን ዶላሩን ፋይናንስ እንዲያደርግ እና ቀሪውን ከአበዳሪ ተቋማት ለማፈላለግ የሚያስችል ስምምነት በቅርቡ መፈረሙ ይታወሳል።

✈️ የመጀመሪያ ምዕራፍ የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ሲጠናቀቅ 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። የግንባታው ሁለተኛ ምዕራፍ ለአውሮፕላን ማረፊያው በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይፈጥራል።

👉 በ4 ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው የአውሮፕላን ማረፊያ፤ ሁለት ዘመናዊ ተርሚናሎች፣ ሁለት የአውሮፕላን መንደርደሪያዎች፣ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል፣ የካርጎ ማስተናገጃ ማዕከል፣ የበረራ መቆጣጠሪያ፣ የመንገደኞች ማስተናገጃዎች፣ ዘመናዊ ሆቴሎች እና መዝናኛዎች እንዲሁም የንግድ ማዕከላት ይኖሩታል።
Spitnik

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.