Logo
Getu Temesgen
“ራይስ የሚደርስ አይመስለኝም” - ሚኬል አርቴታ
#ethiopia | የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አማካዩ ዴክላን ራይስ ቅዳሜ ከበርንማውዝ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ ስለመድረሱ እስካሁን እርግጠኛ አለመሆናቸውን ገለጹ።

አሰልጣኙ ከጨዋታው አስቀድሞ በሰጡት መግለጫ፤ ራይስ በጨዋታው ላይ ስለመሰለፉ ተጠይቀው “እስካሁን አናውቅም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። አክለውም “ገና የልምምድ ጊዜ አለን፤ የአካሉ ሁኔታ እንዴት እንደሆነ እናያለን፤ የአስቶን ቪላ ጨዋታ ለእሱ ፈጥኖበት ነበር” ብለዋል።

የተጫዋቾች ጉዳት 🔎

ከዴክላን ራይስ ጥርጣሬ በተጨማሪ አሰልጣኝ አርቴታ ሁለት ተጫዋቾች ከጨዋታው ውጪ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፦

* ሪካርዶ ካላፊዮሪ እና ሞስኬራ ነገ ከበርንማውዝ ጋር በሚደረገው ፍልሚያ እንደማይሰለፉ ታውቋል።

አርሰናል በሊጉ ያለውን የደረጃ ፉክክር ለማጠናከር በዚህ ጨዋታ ድል ማድረግ ቢጠበቅበትም፣ የቁልፍ ተጫዋቾች በጉዳት መታጣት ለአሰልጣኙ ፈተና እንደሚሆንባቸው ተገምቷል። መድፈኞቹ የራይስን የመጨረሻ የጤና ሁኔታ ተከታትለው በመሰለፍና ባለመሰለፉ ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#arsenal #coyg #declanrice #mikelarteta #premierleague #injuryupdate #bournemouthvsarsenal #footballnews

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.