በዘመናዊው ዓለም ስልክ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ቢሆንም፣ አጠቃቀማችንን ካልገደብን ግን በጤናችን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው። ከመጠን በላይ ስክሪን ላይ መቆየት ከዓይን ድካም እና ከራስ ምታት አልፎ ለከፍተኛ ደም ግፊት፣ ለልብ ችግር እና ለሥነ-ልቦናዊ ቀውሶች (እንደ ጭንቀትና ድብርት) ሊያጋልጠን ይችላል።
በተለይ ማታ ማታ ስልክ መጠቀም የእንቅልፍ ሆርሞንን በማዛባት ለእንቅልፍ ማጣትና በቀን ውስጥ ለሚሰማ የድካም ስሜት ዋነኛ መንስኤ ይሆናል።
ጤናማ የስልክ አጠቃቀም እንዲኖረን ባለሙያዎች የተለያዩ መፍትሔዎችን ይጠቁማሉ። ከእነዚህም መካከል በየ20 ደቂቃው ለ20 ሰከንድ ያህል 20 ጫማ ርቀት ላይ ያለን ነገር በመመልከት ዓይንን ማሳረፍ (20-20-20 Rule)፣ ስልክን ከዓይን በ40-60 ሴ.ሜ ርቀት ላይ መያዝ እና በጨለማ ከመጠቀም መቆጠብ ተጠቃሽ ናቸው። እንዲሁም የአንገትና የጀርባ ሕመምን ለመከላከል ስልክ ስንጠቀም አቀማመጣችንን ማስተካከልና አንገታችንን ለረጅም ሰዓት ዝቅ አለማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው።
ባጠቃላይ በቀን ውስጥ ከ2 እስከ 4 ሰዓት ስክሪን ላይ ማሳለፍ ለጤና ተስማሚና ሚዛናዊ የሚባል ሲሆን፣ ከ8 ሰዓት በላይ መቆየት ግን ለከፋ የጤና መታወክ ይዳርጋል። ስለሆነም ከመተኛታችን ቢያንስ ከ1 እስከ 2 ሰዓት በፊት ስልክን በማስቀመጥ እና የ"Night Mode" አማራጮችን በመጠቀም የአእምሮና የዓይን ጤናችንን መጠበቅ ይኖርብናል። ጤናማ የስክሪን ጊዜን ማላመድ ለተሻለ ምርታማነትና ለተሟላ የጤና ሕይወት ወሳኝ እርምጃ ነው።
ዩቲዩብ ቻናላችንን subscribere ያድርጉት
👉 https://youtube.com/zenas...
zena_science

9 months ago