እግረኞች ተገቢ ባልሆነ የመንገድ አጠቃቀም የሕግ ተጠያቂነት እንደሚደርስባቸው ያውቃሉ?
#ethiopia | የትራፊክ አደጋ በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። ይህ አደጋ ለአካል ጉዳተኝነትና ሕይወትን እስከማጣት የሚያደርስ ከባድ ዋጋ ያስከፍላል።
ለትራፊክ አደጋ ዋነኛው ምክንያት የአሽከርካሪዎች ስህተት እንደሆነ ቢነገርም፣ በእግረኞች በኩል የሚታዩ ክፍተቶችም ሚናቸው ላቅ ያለ ነው።
የኮሪደር ልማት ሥራዎች መንገዶችን ለእግረኞች ምቹ እንዲሆኑ አስችለዋል፤ ሆኖም ግን አሁንም እግረኞች የተፈቀደላቸውን መሻገሪያዎች ባለመጠቀም ለከፋ ጉዳት ሲዳረጉ ይታያል።
በአስፓልት መሃል መጓዝ፣ በተዘጋጀ የእግረኛ ድልድይ አለመሻገርና የመሳሰሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትም ይስተዋላሉ።
የሕግ ባለሙያና ተመራማሪ የሆኑት አቶ አብዱራዛቅ ነስሩ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የመንገድ ዳር ብረት መዝለልና በተፈቀደው አግባብ አለመጓዝ የሕግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ገልጸዋል።
አብዛኛውን ጊዜ በመኪና አደጋ ጉዳይ አሽከርካሪዎች ብቻ ሲጠየቁ መስማት የተለመደ ቢሆንም፣ የእግረኞች ኃላፊነትም ምን መሆን አለበት የሚለው አብሮ መነሳት እንዳለበት ባለሙያው ጠቁመዋል። ለእግረኛ ቅድሚያ መስጠት ተገቢ መሆኑ ቢታመንም፣ እግረኞችም መብታቸውን ሲጠቀሙ ግዴታቸውን ማክበር እንዳለባቸውም አንስተዋል።
ተሻሽሎ የጸደቀው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016 በእግረኞች ስለሚፈጸሙ የትራፊክ ጥሰቶች እንደሚደነግግ ጠቁመዋል።
ከዚህ በፊት የነበረው ሕግ አሽከርካሪዎች ላይ ብቻ ግዴታ የጣለ እንጂ እግረኞችን የማይከለክል እንደነበርም አያይዘው ገልጸዋል።
በአዲሱ ደንብ መሠረት ጥንቃቄ ሳያደርጉ መሻገር፣ ለተሽከርካሪ በተፈቀደ ቦታ ላይ መገኘት፣ ለእግረኛ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ መንቀሳቀስ፣ በብረት ወይም በግንብ ከታጠሩ ቦታዎች መሻገር እንደሚያስቀጣም አስረድተዋል።
የገንዘብ ቅጣቱ አነስተኛ ቢሆንም፣ አሽከርካሪዎችም የራሳቸው ኃላፊነት እንዳለባቸው ባለሙያው ገልጸዋል።
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ ዋቢ በማድረግ አሽከርካሪዎች አደጋ አድርሰው የእግረኛው ጥፋት ካለበትና በዚህም ምክንያት ሕይወት ቢያልፍ፣ ለአሽከርካሪው የሚወሰነው ቅጣት እንደሚቀንስለትም ባለሙያው አብራርተዋል።
በመሆኑም ከአደጋ ለመጠበቅ እና ከቅጣት ለመዳን እግረኞች ሕግን አክብረው በተፈቀደላቸው መንገድ ብቻ መጓዝ እንዳለባቸው የሕግ ባለሙያው ገልጸዋል።
#ebcdotstream

7 months ago