የመጽሐፍ ምርቃት ግብዣ እና የደራሲው ማንነት
ካህሳይ አብርሃ ብሰራት (አማኑኤል ማንጁስ)
#ethiopia | በ«የአሲምባ ፍቅር ተወዳጅ መጽሐፍ የምናውቃቸው ደራሲ ካህሳይ አብርሃ ብስራት (አማኑኤል ማንጁስ) ሁለተኛ መጽሐፋቸውን «ያልተመለሱ ዳናዎች» ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመርቃሉ።
ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ
ለበለጠ መረጃ፦ 0922356430
በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) (ከሬዲዮ ፋና ፊለፊት-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ)
የመጽሐፍ ምርቃት መርሐ-ግብር ላይበክብር በመገኘት እንዲሳተፉ በአክብሮት እንጋብዛለን።
ነገ ታህሳስ 18 2018 በወመዘክር የሚመረቅ መፅሀፍ አለ። የመፅሀፉ ደራሲ የአሲምባ ፍቅር ደራሲ ሲሆን ካህሳይ ማነው የሚለውንም አቅርበናል።
አባት እናት የሰጡት ስም ካህሳይ አብርሃ ብስራት ይባላል።
የተወለደው በ 1950 ዓ ም በጉሎማክዳ ወረዳ ዓጋሜ አውራጃ በትግራይ ክፍለሃገር ( የአሁኑ ክልል ) ነው ። ወላጆቹ ገበሬዎች እንደመሆናቸው መጠን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አስተዳደጉ በድህነት መሆኑን መደበቅ አይቻልም ። በዛላምበሳ ከተማ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ተከፍቶ አባቱ ሊያስመዘግበው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር መምህር ጸሃዬ የአሁኑ ዶክተር የታችኛው ከንፈሩን ከፍቶ ሲያየው ጥርሶቹ ስላልጎረፉ ዕድሜው አልደረሰም በማለት መለሰው። ዳሩ ግን አያቱ ቄስ ገበዝና የቆሎ ተማሪዎች አስተማሪ ስለነበሩ አብሯቸው እንዲማር ተወስኖ ፊደል በመቁጠር አቡጊዳንና ግዕዝን መማር ጀመረ። ዕድሜ ፈቅዶ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ሲመለስ ፊደሎችን ቆጠረ።
ዘመናዊ ትምህርት ቤት እየተማረ በማታና ቅዳሜ እሁድ የቤተ ክህነት ትምህርት በመከታተል ውዳሴ ማርያምና አንቀጸ ማርያም ጨርሶ ቅዳሴ ሲጀምር ሰባተኛ ክፍል አልፎ አግአዚ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመግባት ዓዲግራት ተጓዘ።
እንዲህ ይላል ካህሳይ"... በክረምት ወቅት ደግሞ ገጠር መጥቼ አባቴን ለመርዳት በእርሻና በእረኝነት የተቻለኝን ያህል ከማበርከት አልተቆጠብኩም። የእርሻ ዘመን ሳስታውስ በጣም የሚያሳስበኝ ሁኔታዎች ነበሩ። በጣም ጥቂት ግለሰቦች ባላባቶችና ባለርስቶች ነን በማለት ሰፊውን የእርሻ መሬት ይዘው ድሃውን ገበሬ ሲያሰቃዩ ማየት የዕለት ተዕለት ተግባር ነበር ። ፍርድ ቤት ቢከድም አመፀኖችን ስለሚደግፍ ድሃው ገበሬ አቤቱታ ቢያቀርብም ሰሚ ያለው ጀሮ አልነበረውም። በዚህ የተነሳ መሬታቸው የተነጠቁ ገበሬዎች መንደራቸውን ለቀው ለስደት ይዳረጉ ነበር።
አንድ ቀን አባቴ ለክስ አዲግራት መጥቶ ጥዋት ተነስተን ለማላውቀው ወፍራም ከተሜ የጓሮ ቤቱን አንኳክቶ ገንዘብ ሲሰጠው አየሁ። በሁኔታው ግራ ተጋብቼ ለምን ብዬ ስጠይቀው ዛሬ የፍርድቤት ቀጠሮ ስላለኝ ዳኛው ጉቦ ካላገኝ መሬቴን ለጠላቴ አሳልፎ እንዳይሰጥ ብዬ ነው እንጂ ወድጄ አይደለም ። የልቤ ፍላጎት ቢሆንማ ላንተ ብሰጥ ይሻለኝ ነበር እያለ በትካዜና በሃዘን ሲገልጽልኝ በነበረው ሥርዓት ከፍተኛ ጥላቻ አሳደረብኝ ። ከዓቅሜ በላይ ለማሰብ ተገደድኩኝ።
ስምንተኛ ክፍል እንደደረስኩኝ ይህንና ሌሎችም የህዝብ ብሶት መፈክር በመያዝ የተማሪዎች ንቅናቄ ከአዲስ አበባ ጀምሮ እኛም ጋር ሲደርስ እኔም በአቅሜ ድንጋይ መወርወር ጀመርኩኝ ። የተማሪዎች ንቅናቄም የአብዛኛው ህዝብ ድጋፍ በማግኘቱ የንጉሰ ነገስቱ ሥርዓት በፍጥነት እየጠፋ ሄደ።። መለዮ ለባሹም ንቅናቄውን ተከትሎ ንጉሱን ከስልጣን በማውረድ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት አቋቁሞ ስልጣኑን አደላደለ። በመቀጠልም ለስልጣኑ የሚቃወሙና የሚያሰጉ ዜጎች የፍየል ወጠጤ በሚል እብሪተኛ ዘፈን በማስቀደም ያለፍርድ የገደላቸውን ሰዎች በመዘርዘር በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ሽብር መፍጠር ጀመረ።
የለውጡን አቀንቃኝና ለዓመታት የተዋደቀን ወጣት የጀመረውን ትግል በሀይል በወታደሮች ስለተቀማ ያለው አማራጭ ብረት ይዞ ለመዋጋት ብቻ ስለነበር ወጣቱ ትውልድ በስሜትና በፍላጎት ወደ ጫካ መጉረፍ ጀመረ። በዚህ ወቅት እኔም ትንሽ አድጌ የአቅሜን ለማበርከት የትግል ስሜትና ንጹህ ልቤን በመተማመን ዓሲምባ መሽጎ ወደ ነበረው የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኣብዮታዊ ሰራዊት ለመቀላቀል ከአንድ ጓደኛዬ ጋር በድቅድቅ ሌሊት ተነስተን ወደ አሲምባ አመራን ። ከሁለት ቀናት ጉዞም ጋራቢኖ በሚባለው የኢሮብ መንደር ላይ ከሠራዊቱ ተቀላቀልኩኝ ። አብሮኝ የተጓዘው ጓደኛዬ ግን ሃሳቡን ቀይሮ ወደ ቤቱ ተመለሰ። በሠራዊቱ ህግና ደንብ ስም መቀየር ስላለበት መስከረም 28 , 1968 ዓ ም ካህሳይ መሆን ቀርቶ ኣማኑኤል ማንጁስ ተብሎ እንዲጠራ ተወሰነ።
በዚህች ታሪካዊት ዕለት ለሁለተኛው የህይወት ምዕራፍ ለመላው ጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ መስዋእትነት ለመክፈል ለመራራው ትግል ለመዘጋጀት ከመሰሎቼ ጓዶች በመጨመሬ የተሰማኝን ደስታና ስሜት ለመግለጽ ይከብደኛል ። በሰራዊቱ ታሪክ የመጀመርያ ስልጠና ወስደን በአጭር ወቅት አጥጋቢ ዕደገቶች አሳይተናል ። ይህ በዚህ እንዳለ ሰራዊቱ በሶስት ግንባሮች ተከፋፍልሎ እኔም የወሎውን ግንባር ተመደብኩኝ ።
ረጅሙ ታሪክ በማሳጠር በሰኔ 28 , 1968 ዓ ም በደረሰብን አደጋ እኔም በዞብል ወረዳ በጉራወርቄ በረሃ ይመር ንጉሴ በተባለው ደግ ገበሬ ምርኮኛ ሆንኩኝ ። በጥይት በጩቤ በፋስና በጦር ጓዶች ህይወታቸውን ስታልፍ የዓይን ምስክር ስለነበርኩኝ እኔም የመጨረሻ ህይወት በየትኛው ሰለባ እያልኩኝ ስጠባበቅ የማረከኝ ገበሬ ግን አይዞህ አይዞህ አትፍራ ብሎ ጀሮየ ላይ ቀስ ብሎ ሲነግረኝ ህልም እንጂ እውነትአልመሰለኝም ነበር ።
ከሁለት ቀን ቆይታ በኃላ ፀጉሬን ላጭቶ አገልድም አስታጥቆ ቅቤ ቀብቶ የወሎ ጫማና ዱላ አስይዞ ወሎ ፈረስ የሚባል አውቶብስ አሳፍሮ በሰላም ውደ መቀሌ ሸኘኝ። ከአራት ቀናት የእግር ጉዞ አሲምባ ለቀጣዩ ተልዕኮና ትግል ደረስኩኝ ። በመቀጠልም በተሰጠኝ ተልእኮና ምድብ የምችለውን ያህል አበርክቻለሁ። በነበረኝ የሥራ ምድብ ከጠቅላይ ወታደራዊና ፖለቲካ አመራሮች ለመሥራትና ለመተዋወቅ በነበረኝ ዕድል ስለ ሰራዊቱ ብዙ ሁኔታዎችን ያለ አቅሜ ለማወቅ ችያለሁ። በሰተመጨረሻም 1970 ዓ ም ሰራዊቱ ትግራይን ለቆ ወደ ኤርትራ ሲያፈገፍግ በነበረው ውዥንብርና መከፋፈል ተስፋ በመቁረጥ አሲምባን ተሰናብቼ በኤርትራ አርነት ግምባር ትብብር ሱዳን በመግባት ከታጋይነት ወደ ስደተኛነት ተሽጋገርኩኝ።
ከሁለት ዓመት የሱዳን ቆይታ በአሜርካ ተራድኦ ድጋፍ የፖለቲካ ጥገኝነት ተሰጥቶኝ በ1980 ዓ ም ባላሰብኩትና ባልጠበቅኩት ዕድል አሜርካ ገባሁኝ ። አሜርካ አገር ስገባ የሚያጋጥመኝን ዕድል ምንም አላውቅም ነበር። ሆኖም ግን የትምህርት ምኞቴን ተሳክቶልኝ 1995 ዓ ም ( from the university of Colorado health sciences department, school of pharmacy) በዲግሪ ተመረቅኩኝ ። በትምህርት እያለሁ የቀጠኝ የክሮገር ካምፓኒ ስመረቅም በቀጥታ በመደበኛ staff pharmacist ለ ኣምስት ዓመታት ከሠራሁኝ በኃላ በፋርማሲ ማናጀር ለ25 ዓመታት በመሥራት በክብር በጡረታ ተሰናበትኩኝ ።
ከትግል ከወጣሁኝ በኃላም በአእምሮዬ ውስጥ ሲመላለስ የነበረው የትግሉ ሕይወት የጓዶች ትዝታ ያሉትም የተዉትም እንዲሁም የህዝቡና መልክዓ መሬቱ ፈጽሞ ከዓይነ ህልናየ መሰወር አቃተኝ ። ከዓመታት በፊት የተከነወነውን ልክ ትናንትና እንደሆነ ድቅን ድቅን ይለኛል ። ብተኛም ህልሜ በረሃ ላይ ጓዶች ሲሰዉ ስንጓዝ ስናወራ ስንራብ ስንጠማ ካልሆነ በስተቀር አእምሮየ ሌላ ለማሰብ አቃተው ።
ከዚህና ከዚህ የተነሳ ብቻ የመጻፍ ችሎታና ልምድ ባይኖረኝም ትዝታየን ከጭንቅላቴ ለማውረድ ብቻ ከአሰርት ዓመታት በፊት' የእሲምባ ፍቅር' በሚል ርእስ አማኑኤል በእግሩ የረገጠው በአይኑ ያየው በእጁ የዳሰውና አብሮውኝ የተጓዙትም የተሳተፉትም ጓዶች በመጨመር በግለ ሰብ ታሪክ መልክ ለአንባብያን አቀረብኩኝ ። ንባቡም ባላሰብኩበት ሁኔታ የህዝቡን ቀልብ በመሳብ ተነባቢ ለመሆን ቻለ። በሦስት ቋንቋዎችም ተተርጉሟል ። በዚህ አጋጣሚ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የላቀ ምስጋናየን ማቅረብ እወዳለሁ" በማለታ ደራሲው ካህሳይ ታሪኩን ተርኮልናል።

7 months ago