Logo
YenetaTube
ከባድ የግድያ ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ በእስራት ተቀጣ!!

ተከሳሽ አንለይ አዲሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ወ.ሀ.ቁ 540 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ሆን ብሎ ሰዉ ለመግደል በማሰብ በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ ሸካ ዞን ቴፒ በቴፒ ከተማ አንድነት ቀበሌ ፃኑ በር ተብሎ በማጠራበት በቀን 18/02/2018 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3፡00 በሚሆንበት ጊዜ ሟች አቶ ታምራት ባህሩን የግራ ጎን ደረቱ ላይ በጩቤ ወግቶ በመግደሉ በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ በፖሊስ ብርቱ ክትትል ገዳይ አንለይ አዲሱን በቁጥጥር በማዋል በሰው እና በሠነድ ማስረጃ በማረጋገጥ ለሸካ ዞን ዐ/ህግ ማስተላፉን የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታምራት ኢሞ አስረድተዋል ።
በመሆኑም በሰው እና በሰነድ ተጠናክረው የሄደውን መዝገብ በመረከብ የሸካ ዞን ዐ/ህግ ግለሰቡ ሆን ብሎ የሰዉ ህይወት ማጥፋት ወንጀል ክስ መስርቶ ለሸካ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቧል ።
ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ከሳሽ የሸካ ዞን ዐ/ህግ እንደ ክሱ አቀራረብ የተፈፀመዉን የግድያ የወንጀል ድርጊት የሰዉ፤የሠነድና የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ሟች በግራ ደረቱ ላይ በጩቤ ደረቱ ላይ ተወግቶ መሞቱን በማረጋገጡን ማስረጃ አቅርቦ አስረድቷል ተከሳሽም ራሱን እድከላከል ብይን የሰጠ ብሆንም ተከሳሹ መከላከል ሳይችል ቀርቷል ፡፡
ግራ ቀኙን ስያከራክር የቆየው የሸካ ዞን ከፍተኛ /ፍ/ቤት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ወ.ሀ.ቁ 540 ስር በወ.መ.ሥ.ሥ.ህ.ቁ 149(1) መሠረት ሐሙስ ታህሳስ 16/04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዋለው ችሎት ተከሳሹን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 3/2017 ዓ.ም በደረጃ 7 በእርከን 9 ላይ ያስተምራል መሰል ወንጀል ፈፃሚዎችንም ያስጠነቂቃል በምል ተከሳሹን ለፖሊስ ምርመራ ከተያዙበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ14ዓመት ፅኑ እንድቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል
በመጨረሻም ከመሠል የወንጀል ድርጊት ህብረተሰቡ ራሱን እና አካባቢውን እንድጠብቅ መልዕክታችን ነዉ ።
"የዜና ችሎቱን ዝርዝር ሪፖርት የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ ታክቲክ ወንጀል ምርመራ ስሆን ዘገባው የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ክፍል ነዉ።

ዘገባው የሸካ ዞን ፖሊስ ነው

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.