በናይጄሪያ መስጊድ በሶላት ወቅት ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ 5 ሰዎች ሲገደሉ 35 ሰዎች ቆሰሉ
#ethiopia | በናይጄሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ ቦርኖ ግዛት ሀሙስ በምሽት ሰላት ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሲገደሉ 35 ያህል ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የፖሊስ ቃል አቀባይ ኤኤስፒ ናሆም ዳሶ ኬኔት የማህበራዊ ሚዲያ ድረ-ገጽ በሆነዉ ፌስቡክ ላይ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
በመግለጫው መሰረት፣ ባለስልጣናት በግዛቱ ዋና ከተማ ማይዱጉሪ የተፈጸመው ፍንዳታ በአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ነው ብለው እንደሚጠረጥሩ በማንሳት ምስክሮች ከሰጡት ቃል እና በአጥፍቶ ጠፊነት ከተጠረጠረው ልብስ ውስጥ ቁርጥራጮች መገኘታቸውን ገልጸዋል።
ኃላፊዎቹ የችግሩን መንስኤና ሁኔታ ለማወቅ ምርመራውን ቀጥሏል ብለዋል ።የቦርኖ ግዛት ለዓመታት በታጣቂዉ ቦኮ ሃራም እና መሰል ቡድኖች ስትታመስ ቆይታለች። #dagu

6 months ago