Logo
Getu Temesgen
አብዛኛዎቹ ሩሲያውያን የዩክሬን ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ አንድ ጥናት አረጋገጠ
#ethiopia | አብዛኛዎቹን ሩሲያውያን በዩክሬን ያለው ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ የመንግስት የምርምር ማዕከል ያስታወቀ ሲሆን የሩስያ ሀይሎች በጦር ሜዳ ላይ የሚያደርጉት ግስጋሴ ቢቀጥልም በኪየቭ እና በሞስኮ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከሩሲያ ህዝብ የተሰበሰበዉ አስተያየት እንዳመላከተዉ በወጪው አመት ሩሲያውያን ጦርነቱ እንደሚያበቃ ብሩህ ተስፋ እንዳላቸዉ ተመላክቷል፡፡

ጥናቱን የሰራዉ ቪቲሲኦኤም የተሰኘዉ ማዕከል ምክትል ኃላፊ ሚካሂል ማሞኖቭ በዓመት መጨረሻ ላይ ሆነዉ እንደተናገሩ በጥናቱ ከተካሄደባቸው 1,600 ሰዎች መካከል 70 በመቶው ለሩሲያ 2026 “የተሳካ” ዓመት እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ ብለዋል።

ለብሩህ ተስፋ ዋናው ምክንያት በፕሬዚዳንት ፑቲን ከተገለጹት ብሄራዊ ጥቅሞች ጋር በተገናኘ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻውን ማጠናቀቅ እና የተገለጹትን ዓላማዎች ማሳካት ይቻላል የሚል ተስፋ አድርገዋል፡፡

ማሞኖቭ እንዳሉት የሩስያ ጦር በዩክሬን እያካሄደ ያለውን ጥቃት፣ ዋሽንግተን የዩክሬንን ጦርነት ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኗ እና የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ሚናን ሙሉ በሙሉ ለመተካት አለመቻሉ በገንዘብ እና በወታደራዊ ድጋፍ እጥረት ጦርነቱን ለማቆም የመጨረሻው ስምምነት ከሚጠበቀው ቁልፍ ምክንያቶች በስተጀርባ ይገኛል ሲሉ ጠቁመዋል ።

በግጭቱ ማጠቃለያ ላይ የሩሲያ ወታደራዊ ዘማቾችን ወደ ህብረተሰብ መመለስ እና በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ የዩክሬን ክልሎችን እንዲሁም የሩሲያ የድንበር አካባቢዎችን እንደገና መገንባት ዋና ዋና ጉዳዮች ይሆናሉ ሲሉ ማሞኖቭ አክለዋል። #dagu

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.