Logo
Getu Temesgen
ሰው መኾን የደከመው
#ethiopia | እንግሊዛዊው ቶማስ ትዋይትስ ከልጅነቴ ጀምሮ አስበው ነበር ያለውን ለመተግበር ቆርጧል።

የዜናው ምንጭ ኢንዲፔንደንት ከራሱ ከአቶ ከቶማስ ትዋይትስ ሰማሁት ብሎ እንደነገረን፥ ትዋይትስ ገና የ9 ዓመት ሕጻን ሳለ በጠዋት ከእንቅልፉ ተቀስቅሶ ወደ ትምህርት ቤት መኼድ አስመርሮታል፤ ምነው ድመት በሆንሁና ትምህርት በቀረልኝ፣ እንደልቤ በተኛሁ ብሎ ይመኝ ነበር።

አሁን ካደገ በኋላም ቢኾን ሰው መኾንን ማምለጥ፣ ከሰውነት ዕረፍት ማድረግ ቢቻል ብሎ ዳግም የተመኘው በአንድ አጋጣሚ ነው፥ አንድ ዘመዱ ለሥራ ከመንደሬ ስለምርቅ ውሻዬን ተንከባከብሎኝ ሲል ጠየቀው።

በአደራው መሰረት ውሻውን ሲንከባከብም በድጋሚ ያ የልጅነት ምኞቱ ተቀሰቀሰበት፥ እንስሳት ምንም ዐሣብ የለባቸውም፣ ቤት ኪራይ አይከፍሉም፣ የሥራ ደርሶ መልስ ብሎ ነገር የለባቸውም፣ መብላት መጠጣትና መተኛት ብቻ ነው።

ይህን ዓለም መኖር አለብኝ፣ የልጅነት ሕልሜም ተዳፍኖ አይቀርም ብሎ የቆረጠው ትዋይትስ ታዲያ በፕላስቲክ የተሠሩ ኮቴ፣ ቀንድ፣ አፍ ይዞ አልፕስ ተራራን ወጣ፥ የያዛቸውን ቁሶች አጥልቆም ከፍየል መንጋ ተቀላቀለ።

እንደ እነርሡው ሣር እየበላ፣ ፍሣሽ ውኃ እየጠጣ ለ3 ቀናት አብሯቸው ቆይቶ ሲመለስም GoatMan: How I Took A Holiday From Being a Human የተሰኘ መጽሐፍ ጽፏል።

ሰሚ ባገኘ ቁጥርም የፍየል ዓለም በጣም አስደሣች ነው ብሎ እንደሚናገር የዘገበልን ኢንዲፔንደንት ነው ያለው ትርታ ኤፍ ኤም ነው።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.