Logo
Getu Temesgen
ሩሲያ በአስር ዓመታት ውስጥ በጨረቃ ላይ የኒውክሌር ሀይል ማመንጫ ለመትከል ማቀዷን አስታወቀች
#ethiopia | ሩሲያ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ውስጥ የጨረቃን የጠፈር መርሃ ግብሯን በማስቀጠል የኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያን በጨረቃ ላይ ለመትከል አቅዳለች። ዋናዎቹ የዓለም ኃያል ሀገራት የምድርን ብቸኛ የተፈጥሮ ሳተላይት ለመቃኘት እየተጣደፉ ይገኛል።

እ.ኤ.አ. በ 1961 የሶቪየት ኮስሞናዊት ዩሪ ጋጋሪን ወደ ህዋ በመላክ የመጀመሪያው ሰው ከሆነ ወዲህ ሩሲያ በህዋ ምርምር ላይ ቀዳሚ ሃይል ነበረች።

ከቅርብ አስርት አመታት ወዲህ ግን ከአሜሪካ እና ቻይና ስር ለመከተል ተገዳለች።እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2023 የራሺያ ፍላጎት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን ሰው አልባው ሉና-25 ተልእኮ ወደ ጨረቃ ላይ ለማረፍ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

በአንፃሩ ኤሎን ማስክ የጠፈር ተሽከርካሪዎችን በማምጠቅ ላይ ለውጥ አሳይቷል። የሩሲያ ግዛት የጠፈር ኮርፖሬሽን ሮስኮስሞስ በ2036 የጨረቃ ሃይል ማመንጫ ለመገንባት አቅዶ ከላቮችኪን ማህበር ኤሮስፔስ ኩባንያ ጋር ውል መፈራረሙን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሮስስኮስሞስ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው አላማ የሩስያን የጨረቃ መርሃ ግብር ማለትም ሮቨርስ፣ ኦብዘርቫቶሪ እና የጋራ የሩሲያ-ቻይና አለም አቀፍ የጨረቃ ምርምር ጣቢያ መሠረተ ልማትን ማጎልበት ነው ብሏል።

"ፕሮጀክቱ በቋሚነት የሚሰራ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያን ለመፍጠር እና ከአንድ ጊዜ ተልዕኮዎች ወደ የረጅም ጊዜ የጨረቃ ፍለጋ መርሃ ግብር ለመሸጋገር ጠቃሚ እርምጃ ነው" ሲል በመግለጫው አክሏል።
#dagu

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.