Logo
FIDEL POST NEWS
በሐድያ ለአቅመ ሔዋን ያልደረሰች የገዛ ልጁን አስገድዶ የደፈረ አባት 19 ዓመት እስር ተፈረደበት

👉ተደፋሪዋ ልጅ  ፀንሳለች

ሽፋ ሞሳ የተባለ አባት ግንቦት 30/2017 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 5:ዐዐ ሰዓት አካባቢ አናቱ ቤት ተቀምጦ  የከሰል ፍም አምጭልኝ በማለት ታዳጊዋን ልጅ አዘዘ።

ልጅም  የአባቷን ትዕዛዝ ተግባራዊ በማድረግ የከሰል ፍሙን ባመጣችበት ወቅት  ከውስጥ በሩን በመቀርቀር በቢላዋ በማስፈራራትና በሽርጥ  አፏን በማፈን በራሱ ልጅ ላይ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል መፈፀሙን በማስረጃ ተረጋግጦበታል።

ተደፋሪዋ ልጅ የመራቢያ አካል አከባቢ የቆየ አካላዊ ጉዳት እና የ19 ሳምንት ነፍሰጡር መሆኗን ከሆሳዕና ንግስት እሌኒ መሓመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተደረገው የምርመራ ውጤት ያሳያል።

የአንሌሞ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት እንደዘገበው ተከሳሹ ታዳጊ ልጅ አስገድዶ በመድፈርና  በዘመድ መካከል የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈፀም በሚሉ ክሶች የ19 አመት አስር ተፈርዶበታል።

ድርጊቱ የተፈፀመው በሐድያ ዞን በአንሌሞ ወረዳ  በአጫሞ ከተማ ልዩ ስሙ መገናኛ ተብሎ በሚጠራት ቦታ ነው።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.