Logo
YenetaTube
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባልታወቀ ምክንያት በተነሳ እሳት ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ መውደሙ ተገለጸ።

በደቡብ አፍሪካ የቬንዳ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን በቃጠሎ አደጋ መውደሙ ተሰምቷል።

በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት የምትገኘው የቬንዳ ቅዱስ ሩፋኤል መቃኞ ቤተክርስቲያን በትላንትናው ዕለት በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መውደሟ ተረጋግጧል።

ቃጠሎው የተነሳው በሌሊት በመሆኑና በወቅቱ እርዳታ ማግኘት ባለመቻሉ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የነበረው ንብረት ሁሉ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአደጋው መነሻ እስካሁን አልታወቀም።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለያሬድ በአደጋው ሥፍራ ተገኝተው ምእመናንን አጽናንተዋል ።
ይህ በመንፈሳዊ አገልግሎቱና በምዕመናን አንድነት የምትታወቀው ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰው አደጋ በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ታላቅ ሃዘን ሆኗል።

© Eotc Medhanalem

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.