Logo
Getu Temesgen

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ክልሎች የሰላም ጉባዔ
#ethiopia | የ2050 የተባበሩት መንግስታት ደህንነት ምክር ቤት ድንጋጌዎችን (UNSCR) ተከትሎ በኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ ያሉ ወጣቶች፤ “ወጣቶች ለሰላም” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ በመሰባሰብ ውይይቶችን ያደርጋሉ ፤ ልምድ ይለዋወጣሉ እንዲሁም የተለያዩ የሰላም አጀንዳዎችን ይቀርፃሉ፡፡

በተጨማሪም የክልሎች ወጣቶች የሰላምና ደህንነት ጉባኤ በወጣቶች ሰላምና ድህንነት አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ፤ ትርጉም ያለው የወጣቶች ተሳትፎ እንዲጠናከር አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ፤ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ሰላምና ደህንነት ዕቅድ ዝግጅት ቀጥተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

በቅንጅታዊ ምክክርና በስነጥበብ ሰላምን በመግለፅ ከመንግሰት ፤ ከሲቪል ማህበረሰብ እና ከልማት አጋሮች ጋር በሚደረጉ የፖሊሲ ውይይቶች ወጣቶች በግጭቶች የሚጎዱ አካላት ብቻ ሳይሆኑ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ዋነኛ ተዋንያን መሆናቸው ይረጋገጣል፡፡

በጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ፤ በኖርዌይ ቤተ ክርስቲያን የእርዳታ ድርጅት ፤ በዩቡንቱ የወጣቶች ሰላም ግንባታ ጥምረት ፤ በኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት እና በሌሎች አጋሮች ትብብር የተዘጋጀ፡፡

ሀዋሳ ፤ ኢትዮጵያ
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.