Logo
FastMereja
ተወዳጇ ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ በድል ወደ ሀገሯ ተመለሰች!!

ኢትዮጵያዊቷ የሙዚቃ ኮከብ ቬሮኒካ አዳነ በምስራቅ አፍሪካ የኪነ-ጥበብ መድረክ ላይ ደምቃ በመታየትና አሸናፊነትን በመጎናፀፍ ወደ ትውልድ ሀገሯ ተመልሳለች። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቤተሰቦቾ ፣ወዳጆቾ፣ እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ሚዲያዎች በመገኘት በደማቅ አቀባበል ተቀብለዋታል።

ዝነኛዋ ድምፃዊት በታንዛኒያ በሚካሄደው "2025 Zikomo Africa Awards" ላይ በአራት የተለያዩ ዘርፎች በመታጨት ለሽልማት ስነስርዓቱ ዳሬሰላም ገብታ የነበረ ሲሆን ዛሬ ደሞ ወደ ሀገሯ በአሸናፊነት ዋንጫዎችን ይዛ በደስታ ተመልሳለች።

* የመድረክ ዝግጅት፦
በቅርቡ "መጠሪያዬ" የተሰኘውን ተወዳጅ አልበሟን ያስመረቀችው ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ በሽልማት መድረኩ ላይ ድንቅ ስራዎቿን ማቅረብ ችላለች።

* የአምባሳደርነት ሚና፦
ይህ እጩነት የቬሮኒካን የጥበብ ትጋት ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በምስራቅ አፍሪካ ከፍ አድርጎ የሚያሳይ ነው።

"ይህ ስኬት ለጥበብ ስራዋ ያላትን ትጋት የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በታንዛኒያ መድረክ ሀገሯን ወክላ ላሳየችው ብቃት ኩራት ተሰምቶናል።"

ጥቂት ስለ ዚኮሞ አዋርድ
ዚኮሞ አዋርድ (Zikomo Awards)
በአፍሪካና ካሪቢያን ያሉ በሙዚቃ፣ ፊልም፣ ፋሽን፣ ሚዲያ እና ማህበራዊ ተፅዕኖ ዘርፎች ውስጥ የተለዩ ስኬቶችን የሚያከብር ዓለም አቀፍ ሽልማት ነው።
“Zikomo” በቻቺዋ (Chichewa) ቋንቋ “እናመሰግናለን / Thank you” ማለት ሲሆን፣ ይህ ሽልማት ለተለዩ አርቲስቶችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ክብር ለመስጠት ተመሥርቷል።

ዚኮሞ አዋርድ በየዓመቱ በተለያዩ ሀገራት ይካሄዳል፣ እና የአፍሪካ ፈጠራና ብቃትን ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ያወጣል።

🇪🇹 የቬሮኒካ ሪከርድ በዚኮሞ አዋርድ 🇪🇹
1️⃣ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊት አርቲስት
ቬሮኒካ አዳነ
👉 በZikomo Africa & Caribbean Awards ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ አርቲስት ሆና ተመርጣ ተወዳዳሪ ሆነች።
2️⃣ በአንድ ዓመት 4 ዋና ምድቦች በአንድ ጊዜ መመረጧ ለኢትዮጵያ አርቲስቶች በZikomo ውድድር ላይ አዲስ ሪከርድ ነው።
የተመረጠችባቸው ምድቦች፦
• Best Female Artist of the Year
• Best Performing Artist of the Year
• Best Inspirational Woman of the Year
• Best Song of the Year(Kante Lela)
3️⃣ ሙዚቃ + ማህበራዊ ተፅዕኖ በአንድ ዓመት
• በሙዚቃ (Song / Performance)
• በማህበራዊ ተፅዕኖ (Inspirational Woman) ምድቦች መመረጧ
➡️ Zikomo ላይ አርቲስትነትና አመራርን አንድ ላይ ያጣመረ ልዩ ሪከርድ ነው።
4️⃣ የኢትዮጵያ ሙዚቃን ወደ Zikomo መድረክ ያመጣች።
👉 Zikomo በዋናነት የደቡብ እና ካሪቢያን አገራት የሚታወቅ መድረክ ሲሆን
👉 ቬሮኒካ የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዚህ መድረክ በግልጽ ሁኔታ የተወከለችበትን መጀመሪያ መድረክ አሳየች። ለኢትዮዽያ አርቲስት በር ከፈተች
5️⃣ በብዙ አገራት አርቲስቶች መካከል ኢትዮጵያዊ ሴት አርቲስት ሆና እንደ ዋና ተወዳዳሪ መታየቷ ለሴቶች አርቲስቶች አዲስ መንገድ ከፈተች።
👉 የኢትዮጵያ ሙዚቃን ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ አወጣች 🇪🇹✨
👏 በድጋሚ እንኳን ደስ አለሽ የኔ ጀግና
ኮርተሽ አኩርተሽናል
ሀገሬ ጀግናሽን አክብሪ
🇪🇹❤️ ኢትዮጵያ ታብራ ❤️

🇪🇹🏆 🏆 ይቀጥላል የአፍሪማ!!!

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.