አሜሪካ በየዓመቱ የምታካሂደውን የዲቪ ሎተሪ አቆመች!
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በብራውን ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመ የጅምላ ጥቃት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የአሜሪካን ግሪን ካርድ ሎተሪን (ዲቪ) አገዱ።ጥቃቱን ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረው እና ሐሙስ ዕለት ሞቶ የተገኘው ፖርቹጋላዊው በአውሮፓውያኑ 2017 ዲቪ ሎተሪ አሸንፎ ወደ አገሪቱ የገባ ሲሆን ግሪን ካርድም ተሰጥቶታል።
የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር የሆኑት ክሪስቲ ኖም "በዚህ አስከፊ ፕሮግራም አሜሪካውያን ከእንግዲህ እንዳይጎዱ ለማረጋገጥ" በሚል ትራምፕ በሰጡት መመሪያ መሠረት የቪዛ መርሃ ግብሩን ለጊዜው እንዲቋረጥ መደረጉን ተናግረዋል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተጠርጣሪው የ48 ዓመቱ ክላውዲዮ ኔቭስ ቫለንቴ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ፕሮፌሰር ኑኖ ሉሬሮንም ገድሏል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
የዲቪ ሎተሪ ፕሮግራሙ በአሜሪካ በስደተኝነት በቂ ድርሻን ላላገኙ አገራት ዜጎች በየዓመቱ 50 ሺህ ቪዛዎችን ይሰጣል። ይህ ደግሞ የአሜሪካ ዜግነትን ለማግኘትም በር ከፋች ነው።ኖም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ትራምፕ ቀደም ሲል በኒው ዮርክ ከተማ ስምንት ሰዎች በጭነት መኪና ተገጭተው ከተገደሉ በኋላ ፕሮግራሙን ለማስቆም "ታግለዋል" ብለዋል።
ኖም እንዳሉት የኡዝቤኪስታን ተወላጅ የሆነው ሳይፉሎ ሳይፖቭ፣ የኢስላሚክ ስቴት ደጋፊ የሆነ እና ለተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ግለሰብ በዲቪ1 ፕሮግራም መሠረት ወደ አሜሪካ ገብቷል።
seledadotio

6 months ago