በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማምሻውን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ
#ethiopia | በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ ማምሻውን በደረሰ የተሽከርካሪ መገልበጥ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት አመሻሽ ላይ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የተሽከርካሪው ረዳት ጨምሮ የሰባት ወንድ እና የሁለት ሴቶች በአጠቃላይ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አልፏል።
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 06860 ድሬ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ለግዜው በውል ያልታወቀ ተሳፋሪን አሳፍሮ ከቀርሳ ከተማ ወደ ማያ ከተማ ሲጓዝ ቀርሳ ወረዳ አዋ መራ ቀበሌ ሲደርስ ቀርሳ ድልድይ ውስጥ ገብቶ አደጋው መድረሱ ተገልጿል ።
ህይወታቸውን ካጡ ዘጠኝ ሰዎች በተጨማሪ በአራት ሰዎች ላይ ከባድ ፣በሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል አደጋ መድረሱን ገልፀዋል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ቢሆንም አሽከርካሪው ተሳፋሪን ከእቃ ጋር ከመጠን በላይ በመጫን የተከሰተ ሳይሆን እንዳልቀረ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ጨምረው ገልፀዋል ። አሽከርካሪው ከአደጋው ቦታ ተሰውሮ ያመለጠ ሲሆን ፖሊስም በክትትል ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። #dagu

6 months ago