Logo
FastMereja
መደመር፣ ብልጽግና እና ኮሪደር አሸናፊን ተዋወቋቸው

መምህር አሸናፊ ታደሰ ይባላሉ – የሶስት ልጆች አባት ናቸው። ለልጆቻቸው ያወጡላቸው አስገራሚ የስም ስያሜ ግን ለሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች መነጋገሪያ ከሆነ ውሎ አድሯል። መምህሩ ለልጆቻቸው ያወጡላቸው ስያሜ ግን ብዙዎቻችን እንደምናደርገው የቤተሰብ መታሰቢያን፣ ሃይማኖታዊ ትርጉምን ወይም የቃላትን ውበት ላይ ተመርኩዘው አይደለም። በአንጻሩ “ስም ማለት የታሪክ ማሕደር፣ የጊዜ መዝገብና የቆሙለት ዓላማ መገለጫ ነው” የሚለው ርዕዮተ ዓለማቸውን እንዲሸከም አድርገው ነው።

መምህር አሸናፊ የታሪክ ሰነድ እንዲሆን ለልጆቻቸው ያወጡላቸው መጠሪያ “መደመር”፣ “ኮሪደር” እና “ብልጽግና” ሆኗል።

የመጀመሪያ ልጃቸው የተወለደችው ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም። ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስቀል አደባባይ ከተደረገው የመደመር መንግስት የድጋፍ ሰልፍ በኋላ ነበር። እናም “መደመር ለኢትዮጵያ ተስፋ ነው” በሚል እምነት ለበኩር ሴት ልጃቸው መደመር አሸናፊ የሚል ስያሜ ሰጧት።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 2013 ዓ.ም. በተካሄደ ማግስት ደግሞ ሁለተኛ ልጃቸው ይህቺን ምድር ሲቀላቀል መምህር አሸናፊም “ብልጽግና ከፓርቲ ስም በላይ ማደግና መለወጥ ነው” በሚል አመክንዮ ብልጽግና ብለው መጠሪያ ለወንድ ልጃቸው አወጡለት።

አዲስ አበባ ላይ ጀምሮ በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች የተጀመረውን የኮሪደር ልማትና የከተሞችን ውበት ለመዘከር ሲሉ ደግሞ ሶስተኛዋ ሴት ልጃቸውን ኮሪደር ብለው ጠሯት።

Via: AMN

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.