ናይጄሪያዊዉ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ከነዳጅ ተቆጣጣሪ አካል ጋር ግጭት ዉስጥ ገቡ
#ethiopia | የናይጄሪያ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት አሊኮ ዳንጎቴ እሁድ እለት ከነዳጅ ተቆጣጠሪ አካል ጋር ያለውን ውዝግብ ጋር ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
በናይጄሪያ የሚገኙ የነዳጅ ማጣሪያዎችን አደጋ ላይ የሚጥል ርካሽ ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ አድርገዋል ሲሉ ዳንጎቴ ከተቆጣጣሪዉ አካል ጋር ያላቸዉን ልዩነት ገልጸዋል፡፡ናይጄሪያ በአፍሪካ ትልቁ የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገር ብትሆን ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ ናት፡
፡ይህንኑ ችግር ለመቀየት የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።ዳንጎቴ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ቁጥጥር ካልተደረገባቸው ለሥራ፣ ለኢንቨስትመንትና ለኢነርጂ ደህንነት ስጋት ይሆናሉ ብለዋል።
በሌጎስ በሚገኘዉ እና በቀን 650 ሺ በርሜል የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ ንግግር ያደረጉት ዳንጎቴ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች “የአገር ውስጥ አቅምን ለመፈተሽ” ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፣ ይህም ናይጄሪያ ወደ ኢንዱስትሪ ለምታደርገዉ ሽግግር ፈተና እየሆነ ይገኛል ብለዋል፡፡
ዳንጎቴ የናይጄሪያ ሚድ ስትሪም እና ዳውንስትሪም ፔትሮሊየም ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ኃላፊ ፋሩክ አህመድን በተመለከተ በዘርፉ ያላቸውን የአስተዳደር ስጋት እና የግል ወጪዎች ከህጋዊ ገቢ በላይ ናቸው በሚል ክስ ላይ ይፋዊ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
አህመድ በሚመሩት ተቋማት ላይ ለቀረበዉ አስተያየት ወዲያውኑ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም የዳንጎቴ ማጣሪያ በፔትሮሊየም ምርቶች ሽያጭ ላይ በብቸኝነት መያዝ እንደሚፈልግ ተናግረዉ ነበረ፡፡ የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካው ምርት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሊያሟላ አይችልም ሲሉ ተደምጠዋል።
#dagu

6 months ago