አርሰናል እዚህ ነው!
* ወሳኙ የአርሰናል ድልም ዕድልም፤
ሊቨርፑል ከMo ጋር አሸንፏል !
#ethiopia | የወርሃ ታህሳስ ከቪላ ፓርክ የጀመረ የመድፉ ዕርግማን አርሰናልን ወስዶ መለሰ ። የሊጉ ውራ ዎልቭስ ኤምሬትስን ፀጥ ረጭ ባደረገ ቅፅበት መድፉ ወድቆ ተነሳ ። ጋብሪል ጄሱስ ለወራቶች ከሜዳ ርቆ የቆየው ብራዚላዊ የሰሜን ለንደኑ ገናና ድንጋጤን ወደ ፈንጠዝያ ቀየረ ። መድፈኛውም ዕጅግ ውዱን 3 ነጥብ ከሊጉ ደረጃ መዳቢ ውራው ዎልቭስ ነጠቀ ። ይህ የአንድ ዕውነተኛ የሻምፒዮን ቡድኖች የላቀ ተጋድሎ ሌላኛው መልክ ነው ። ተቸግሮም በማሸነፍ የፀናው በፍላጎት ታታሪነት ውስጥ የተገኘው የመድፉ ድል ነው ። አንዳንድ ግዜ በሻምፒዮንነት መልክ የተቃኙ ቡድኖች ከጥንካሬ ጥረታቸው ባሻገር ለድላቸው መፅናት ዕድልም እንደሚያስፈልጋቸው አርሰናል ያረጋገጠበት ጣፋጩ ውጤት ነው ። የሊጉ አውራ አርሰናል ክዋክብቶች የአሸናፊነት ሜንታሊቲን የፈተነው የማታ ማታ ግን ኤምሬትስን በደስታ ጩኸት ያቀለጠውም ገድል ነው ። አሰልጣኝ super mike arteta እና ስታፉን እንደ ልጅ በደስታ ያስብረቀው ሌላኛው ቁልፍ የመድፉ የአሸናፊነት ጉዞ ዕርምጃ ነው ። በቡካዮ ሳካ ታላቅ የጨዋታ ተፅእኖ ፈጣሪነት የተጠናቀቀ የጋብሪየል ጄሱስ ማጂክ ነው ። ነሐሴ የሊጉን ውድድር ጀምሮ 16 ተጫውቶ ሁለት ነጥብ ብቻ ያለው የሊጉ ውራ ዎልቭስን ወደ ሶስት ነጥብ ሊያሻግር የነበረው ኤምሬትስን በድን ያደረገ የአቻ ውጤት ድራማን ወደ ድል የቀየረ የGunning for Greatness ሌላኛው ታላቁ አይረሴው ሳምንት ነው ። ለዋንጫ ድል በተቃኙ ቡድኖች ውስጥ የሚታየው የሸርፍራፊ ሰከንዶች ተዐምር ሌላኛውም ቀለም ነው ። ከነገው የፓላስ ሲቲ ጨዋታ በፊት የተመዘገበው የመድፈኛው አርሰናል የወርሃ ታህሣሥ የአሸናፊነት ጉዞን የተለመደ የመንገዳገድ ሜንታሊቲን የበለጠ ከአደጋ ወደ ድል አንድነት የእራስ መተማመን ለመቀየር ታላቅ ሚና ሊጫወት የሚችለውም ውጤት ነው ። ከሶስት ነጥብም በላይ የሆነው መድፉን በደንጋጤ ከወርሃ ዲሴምበር ሀንጎቨሩ ጋር ወስዶ የመለሰው ድል ነው ። ለ11 ወራቶች በጉዳት ከሜዳ ርቆ በከረመው ብራዚላዊ ጋብሪየል ጄሱስ ማጂክ እና ጥቁሩ ቅመም ቡካዮ ሳካ የጨዋታው top of z match ሚና የተመዘገበ የአርሰናል ወሳኙ ድልም ዕድልም ነው ።
በአንፊልድ ሞ ግሬትን ወደ ስኳዱ የመለሰው ሊቨርፑል ዛሬም ከሰፊ የተከላከይ መስመሩ ሚዛን ከጎደለው የቡድን ችግሩ ጋር ብራይተንን 2ለ0 ረቷል ። ከቀዩ ምድር ከመሃመድ ሳላህ ያጦዙት የውዝግብ ኳስን መሬት ያወረዱት አሰልጣኝ አርን ስሎት ተጠባባቂ አድርገው የጀመሩት ኮኮብን የጎሜዝ ጉዳትን ተከትሎ ፈጥነው ወደ ሜዳ አስገብተው ለነገ ጉዟቸው መረጋጋት ታላቅ ሚና ያለው ወሳኝ ውጤትን አስመዝግበው የተጫረው እሳትንም አዳፍነው ወጥተዋል ። አንፊልድም የፈርኦኑ ንጉስን በዝማሬ ተቀብሎ በድል መወድስ ወደ አፍሪካ ዋንጫው የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ግዳጁ ሸኝቷል ። ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ ከMixed zone ዳግም የሚሰጠው አስተያየት እንዳለ ከጋዜጠኞች ዛሬስ የምትናገረው አለ ተብሎ የተጠየቀው መሃመድ ሳላህ ለሁለት ተከታታይ ሳምንት ዕንደገና እንዳታስቡት በማለት ቀልዷል ። ሞ ግሬት የዋዛን ሪከርድ የነጠቀ የፕሪሚየር ሊጉም የሊቨርፑል ታላቁ ሕያው ኮኮቦ መሆኑን ለሁጎ ኢኪቲኬ ሁለተኛ ጎል በፈጠረው ዕድል አሳይቷል ። አሰልጣኝ አርን ስሎቶም ከሻምፒዮንነት ክብራቸው ማግስት ሲበዛ እየተፈተኑ ባሉበት ሲዝን ለመሃመድ ሳላህ ያላቸውን አድናቆት ተናግረዋል ። እርሱ ሁሌም ለሊቨርፑል ከዕንዲህ ዐይነት ድንቅ የውጤት ሚናው ጋር አስፈላጊ ነው ሲሉ ተደምጠዋል ። ሰውየው በተፈጠሩ የትናንቱ ነገሮች ላይ ብዙ የማውራት ፍላጎት እንደሌላቸው አረጋግጠዋል ። ጉዟችን ከመሻሻሎች ጋር ይቀጥላል ። ከሳንሲሮ መልስ የቀጠለ ድላችን የበለጠ በወሳኙ የውድድር ምዕራፍ በወጥነት እንዲቀጥል ጠንክረን መስራታችን ይቀጥላል ሲሉ ተደምጠዋል ።
በገናናው ሊግ የsuper Saturday ጨዋታዎች እየዞረ መሸነፍን ከሰሞኑ ስራው አድርጎት የከረመው ሚስተር ቼልሲ ከice co ኮል ፓልመር ማጂክ ጋር ኤቨርተንን 2ለ0 ረቶ ወደ ድል ተመልሷል ። የበርንሌይ እና ፉልሃም ቀልብ ገዢ ፉክክር በፉልሃም 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል ። የፕሪሚየር ሊጉ የማይገመት ምትሃትም ነገም በsuper sunday ይቀጥላል ። የፓላስ ሲቲ እና የሰንርላንድ ኒውካስል የታይኒሳይድ ደርቢ የሰሜን ምስራቅ እንግሊዝ የማይዋደዱ ጎረቤቶች የምሽት 11:00 ጨዋታዎች ትንቅንቅ ቀልብ ገዢ ናቸው ።
tribune sport

8 months ago