Logo
Getu Temesgen
ሚያሚ በሦስት አስርት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲሞክራት ከንቲባ መረጠች
#ethiopia | ዴሞክራቷ ኢሊን ሂጊንስ ለሚያሚ ከንቲባ ሆና ስትመረጥ ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላ የዲሞክራት ፓርቲ የመጀመሪያ አባል ሆናለች።

የትራምፕ ጠንካራ ድጋፍ ባለባት ፍሎሪዳ እንዲሁም የሂስፓኒክ ነዋሪዎች በሚበዙባት ከተማ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚደገፉትን ሪፐብሊካን አሸንፋለች።

ሲ ኤን ኤን እና አሶሺየትድ ፕሬስ ምርጫው ከተጠናቀቀ ከአንድ ሰአት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሂጊንስ ማሸነፏን ዘግበዋል።

የቀድሞዋ ሚያሚ-ዴድ ካውንቲ ኮሚሽነር የሪፐብሊካን ተቀናቃኛቸውን ኤሚሊዮ ጎንዛሌዝን በ18 በመቶ ብልጫ አዲሷ ከንቲባ አግኝታለች።

ይህ ውጤይ በ2026 የአጋማሽ ዘመን ምርጫዎች በኮንግረሱ ውስጥ የትራምፕን ብቸኛ የበላይነት ለማስጠበቅ ሪፓብሊካን ያላቸውን ተስፋ አደብዟል።

የሂጊንስ ወሳኝ ድል ዲሞክራቶች ባለፈው ወር በምርጫ ካሳኩት ድል ቀጥሎ በፍጥነት የመጣ ስኬት ነው።

እ.ኤ.አ. በ 2024 ትራምፕ ከዴሞክራቶች የነጠቁት የሂስፓኒክ ድጋፍ ከዚያን ጊዜ ወዲህ እየከሰመ ስለመሆኑ ሪፓብሊካኑ ያላቸውን ስጋት ያጠነክራል።

የ61 ዓመቷ ሂጊንስ በፌስ ቡክ አካውንቷ ላይ ባጋራችው መግለጫ የድሏን ሀገራዊ እንድምታ አልተናገረችም ይልቁንም ውጤቱን በአገር ውስጥ ደረጃ "የአመታት ትርምስ እና ሙስና ላይ አዲስ ምዕራፍ " ነው በማለት ገልጻለች። #dagu

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.